Connect with us

የከተማ አስተዳደሩ በደቡብ ክልል ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ላጋጠማቸው ወገኖች 4 ሚሊዮን ብር ሰጠ

የከተማ አስተዳደሩ በደቡብ ክልል በጎርፍና የመሬት መንሸራተት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ሰጠ
Ethiopian Broadcasting Corporation

ዜና

የከተማ አስተዳደሩ በደቡብ ክልል ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ላጋጠማቸው ወገኖች 4 ሚሊዮን ብር ሰጠ

የከተማ አስተዳደሩ በደቡብ ክልል በጎርፍና የመሬት መንሸራተት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ሰጠ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በደቡብ ክልል በጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 4 ሚሊዮን ብር የሚገመት የገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ አበረከተ፡፡

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ 2.5 ሚሊዮን ብር የገንዘብ እና 1.5 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የአይነት በጠቅላላው የ4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ አስረክበዋል፡፡

በርክክቡ ወቅት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት ለወገኖቻችን አብሮነት፣ ፍቅር እና አጋርነትን መግለጽ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ ነው ብለዋል፡፡

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ወደፊትም በክልሉ ካሉ ህዝቦች ጋር ከባህል ትስስር ጀምሮ በእህትማማችነት እና ወንድማማችነት የተጀመረው ትስስር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላደረገው ድጋፍ በደቡብ ህዝቦች ስም ምስጋና ማቅረባቸውን ከከንቲባ ፅ/ቤት ፕሬስ ሰክረተሪ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። (EBC)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top