Connect with us

የ8ኛ እና የ12 ክፍል ትምህርት ጥቅምት 16 ይጀመራል

የ8ኛ እና የ12 ክፍል ትምህርት ጥቅምት 16 ይጀመራል
Addis Ababa education bureau

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

የ8ኛ እና የ12 ክፍል ትምህርት ጥቅምት 16 ይጀመራል

የ8ኛ እና የ12 ክፍል ትምህርት ጥቅምት 16 ይጀመራል

በአዲስ አበባ ዘንድሮ ለ8ኛ እና 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎች የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም   ትምህርት ይጀምራሉ።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ በሰጡት መግለጫ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚያስችሉ ስራዎች በመሰራታቸው የመልቀቂያ ፈተና የሚፈተኑ ተማሪዎች በሁሉም የከተማዋ ትምህርት ቤቶች ከመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር ቀድመው ትምህርት ይጀምራሉ ብለዋል።

የፊታችን ሰኞ ትምህርት የሚጀመርባቸው ትምህርት ቤቶች ላይም የፀረ ተዋህሲ ርጭት መካሄዱንና የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች መከናወናቸውን አቶ ዘላለም አመላክተዋል።

የሙቀት መለኪያና ጭምብልም በሁሉም ትምህርት ቤቶች በመሰራጨት ላይ መሆኑን ቢሮ ኃላፊው አስታውቀዋል።

የ8ኛ እና 12 ክፍል የመልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች 45 ቀን ከተማሩ በኋላ ለፈተና እንደሚቀመጡም የገለጹት አቶ ዘላለም በአዲስ አበባ ከተማና በዙሪያዋ ያሉ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ትምህርት የሚጀምሩት ጥቅምት 30 ቀን 2013 እንደሆነም ሃላፊዉ ተናግረዋል።

ሃላፊዉ እንዳስታወቁት የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ሲባል የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ቅዳሜን ጨምሮ በሳምንት 6 ቀናት እንደሚማሩ እና የተቀሩት ክፍል ተማሪዎችም በቀን ፈረቃ በሳምንት ሶስት ቀን ትምህርት መማር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በከተማዋ 230 ትምህርት ቤቶች ተገንብተው ለአገልግሎት እንደሚበቁና የተማሪዎችን የጤና የሚከታተሉ በ513 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 2052 የጤና ባለሙያዎች ቅጥር መፈፀሙን ሃላፊዉ ተናግረዋል፡፡(አ/አ ኘረስ ሴክረቴሪያት)

 

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top