Connect with us

ሸገር ዳቦ ፋብሪካ በአከፋፋዮች ችግር ምክንያት በቂ ዳቦ ማምረት አልቻልኩም አለ

ሸገር ዳቦ ፋብሪካ በአከፋፋዮች ችግር ምክንያት በቂ ዳቦ ማምረት አልቻልኩም አለ
Photo: Social media

ዜና

ሸገር ዳቦ ፋብሪካ በአከፋፋዮች ችግር ምክንያት በቂ ዳቦ ማምረት አልቻልኩም አለ

ሸገር ዳቦ ፋብሪካ በአከፋፋዮች ችግር ምክንያት በቂ ዳቦ ማምረት አልቻልኩም አለ

በታሰበው ልክ ዳቦን በማምረት ወደ ተጠቃሚው ለማድረስ ያልቻልኩት በፋብሪካው ያልተጠናቀቁ  የኮምሽን ስራዎች በመኖራቸው ነው ሲል ገልጿል።

በቀን ከ 1 ነጥብ  6 እስከ 1 ነጥብ 7 ሚለየን ዳቦ ያመርታል ተብሎ ወደ ስራ የገባው ሸገር ዳቦ ፋብሪካ  በአሁኑ ሰዓት በቀን ወደ 1 ሚለየን ዳቦ  በማምረት ላይ ይገኛል፡፡

የፋብሪካው የኦፕሬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ ኑረዱን ሙዘሚል ለኢትዮ ኤፍ ኤም ይሄን ብለዋል።

ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ እንዳይገባ ምርቱን ወደ ተጠቃሚዎች የሚያከፋፍሉ እና ሌሎች ተያያዥ የኮሚሸን  ስራዎች ሙሉ በሙሉ አልተጠናቀቁም፡፡

ይሁን እንጂ  ፋብሪካው ሲቋቋም ሊያመርት ከታቀደው  አኳያ በአሁን ሰዓት እየተመረተ ያለው ዳቦ መጠነኛ የሚባል እንደሆነም አንስተውልናል፡፡

በፋብሪካው በቀን እየተመረተ ያለው 1 ሚለየን  ዳቦ ለ 363 ማህበራት ተደራሽ እየተደረገ መሆኑንም ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

ይሁን እንጂ ወደ ማህበራቱ ተከፋፍሎ በከተማዋ በሚገኙ የሽገር ዳቦ መሸጫ ሱቆች  ብቻ የሚቀርበው  ይህ ዳቦ በጊዜ ማለቅና በበቂ ሁኔታ ለህብረተሰቡ ያለመድረስ  ችግር መኖሩን  በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውረን ባደረግነው ምልከታ ታዝበናል።(ኢትዮ ኤፍ ኤም)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top