Connect with us

በአዳማ ከተማ ህንጻ ተደርምሶ የአራት ሰው ህይወት አለፈ

በአዳማ ከተማ ህንጻ ተደርምሶ የአራት ሰው ህይወት አለፈ
Ethiopian Broadcasting Corporation

ዜና

በአዳማ ከተማ ህንጻ ተደርምሶ የአራት ሰው ህይወት አለፈ

በአዳማ ከተማ ህንጻ ተደርምሶ የአራት ሰው ህይወት አለፈ

በአዳማ ከተማ ዛሬ ህንጻ ተደርምሶ በደረሰው አደጋ የአራት ሰው ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

የከተማዋ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ለኢዜአ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው በአዳማ ደምበላ ክፍለ ከተማ ኢሬቻ ቀበሌ ውስጥ ነው።

በቀበሌው ልዩ ስሙ ኮሮኔል ደጀኔ ስሜ ትምህርት ቤት አቅራቢያ ያለው ሃዊ ሆቴል በመደርመሱ አደጋው ሊደርስ እንደቻለ አስረድተዋል።

ሆቴሉን በአዲስ ህንፃ ለመተካት አሮጌውን እያፈረሱ ባሉት የቀን ሠራተኞች ላይ በደረሰው አደጋ ከመካከላቸው የአራት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን ኢንስፔክተሯ አስታውቀዋል።

ሁለት ሰዎች ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በአዳማ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

የአደጋው መንስኤ የጥንቃቄ ጉድለት መሆኑንም ኢንስፔክተሯ  መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።(EBC)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top