Connect with us

በመተከል ዞን በንፁሃን ግድያ የተጠረጠሩ 504 ሰዎች ታሰሩ

በመተከል ዞን ንፁኃን እንዲገደሉ በማስተባበርና በመምራት የተጠረጠሩ 504 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ፡፡
Amhara Mass Media Agency

ዜና

በመተከል ዞን በንፁሃን ግድያ የተጠረጠሩ 504 ሰዎች ታሰሩ

በመተከል ዞን በንፁሃን ግድያ የተጠረጠሩ 504 ሰዎች ታሰሩ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በመተከል ዞን ንፁሃን እንዲገደሉ ያስተባበሩና የመሩ 504 ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ገለጹ፡፡ 

የአማራና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች በጉዳዩ ዙሪያ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም በተደጋጋሚ በክልሉ መተከል ዞን በንፁሃን ላይ የሚፈፀመው ጥቃት መንስኤው ብዙ መሆኑን ጠቅሰው፥ የመሬት ይዞታ እና ለውጡን ተከትለው ያኮረፉ አካላት የሚፈጥሩት የፀረ ሰላም ኃይሎች እንቅስቃሴ ዋናዎቹ ናቸው ብለዋል፡፡

አቶ አሻድሊ ከንፁሃኑ ግድያ በስተጀርባም የህወሀት እጅ እንዳለበት ደርሰንበታል ብለዋል፡፡

ይህን ድርጊት ለማስፈፀም ወጣቶችን በመመልመልና አንዳንድ በኢንቨስትመንት የገቡ ባለሀብቶችን በመጠቀም ችግሮቹ እንዲባባስ ህወሃት ስራ ስትሰራ ከርማለችም ነው ያሉት፡፡

የክልሉን ሰላም ወደነበረበት ለመመለስና ጥፋተኞችን ተጠያቂ ለማድረግ በክልሉ ተዋቅሮ ያለውን የኮማንድ ፖስት አፈፃፀም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በመሆን መገምገማቸውንም ነው የተናገሩት፡፡

የመከላከያ ኃይሉ በአካባቢው የመሸጉ ታጣቂ ቡድኖችንና ሽፍታዎችን የመደምሰስ ስራ እየሰራ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል፡፡

የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ከአማራ ክልል የፀጥታ መዋቅር ጋር የጣምራ ስራዎችን እየሰሩ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በበኩላቸው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሚኖሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ነዋሪነታቸው በቤኒሻንጉል ክልል በመሆኑ የክልሉ መንግስት ደህንነታቸውን ማስጠበቅ እንዳለበት አንስተዋል፡፡(FBC)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top