Connect with us

ወ/ሮ ሮማን ገብረ ስላሴ ተሸኙ

ወ/ሮ ሮማን ገብረ ስላሴ ተሸኙ
Photo: Social media

ዜና

ወ/ሮ ሮማን ገብረ ስላሴ ተሸኙ

ወ/ሮ ሮማን ገብረ ስላሴ ተሸኙ

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤትን ከ2008 አጋማሽ ጀምሮ በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ የቆዩት ወ/ሮ ሮማን ገብረ ስላሴ በትላንትናዉ እለት በጽህፈት ቤቱ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡

ወ/ሮ ሮማን የጡረታ መልቀቂያቸዉን ባሰለፍነዉ 2012 ዓመት ለጽህፈት ቤቱ ማስገባታቸዉን በታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀይሉ አብርሃም ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ ሮማን ገብረ ሥላሴ የሕዝቡን ተሳትፎ በሚመለከት በሀገር ውስጥም በውጭም ያለው የሕብረተሰብ ክፍል ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል በርካታ ስራዎችን መስራታቸዉ ይታወሳል፡፡ ህወሓት በፌደራል መንግሥቱ ውስጥ ያላቸውን ሥልጣን እንዲለቁ አስቸኳይ መመሪያ ካቀረበላቸው አባላቶቹ መሀል አንዷ የሆኑት የህዳሴው ግድብ ሕዝባዊ ተሳታፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሮማን ገብረ ሥላሤ  ይህንን ሀሳብ እንደማይቀበሉ መናገራቸዉ አይዘነጋም፡፡

የጡረታ መልቀቂያቸዉን ተቀባይነቱን ማግኘቱን ተከትሎ በዛሬዉ እለት የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ዶ/ር አረጋዊ በርሔን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብ/ም/ቤት  ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አድርጎ መሾሙን አስታዉቋል፡፡ዶ/ር አረጋዊ በርኸ  ትዴት የተሰኘ ፓርቲ ሊቀመንበር መሆናቸዉ ይታወቃል፡፡

(ብስራት ሬድዮ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top