Connect with us

ከ100 ሺ ብር በላይ የብር ለውጥ ቀነ ገደብ በነገው ዕለት ይጠናቀቃል

ከ100 ሺ ብር በላይ የብር ለውጥ ቀነ ገደብ በነገው ዕለት ይጠናቀቃል
Photo: Social media

ዜና

ከ100 ሺ ብር በላይ የብር ለውጥ ቀነ ገደብ በነገው ዕለት ይጠናቀቃል

ከ100 ሺ ብር በላይ የብር ለውጥ ቀነ ገደብ በነገው ዕለት ይጠናቀቃል

ከ100ሺህ እስከ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የብር ኖቶት ቅያሬ ቀነ ገደብ በነገው ዕለት ( ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም) ይጠናቀቃል፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን ገንዘባቸውን መቀየር ያልቻሉ ወገኖች በቀሪው ጊዜ እንዲጠቀሙ  የኢትዮጵያ ብሔራዊ  ባንክ በተደጋጋሚ አሳስቧል፡፡

ከ100ሺ ብር በታች ላለው ገንዘብ ለመቀየር  የተሰጠው ቀነ ገደብ ሶስት ወራት ሲሆን ቀሪ ሁለት ወር ገደማ ይቀረዋል፡፡

በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነባሩን በአዲሱ ብር ለመተካት እየተካሄደ ባለው እንቅስቃሴ፣ ከ90 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ አዲሱን ብር ማሠራጨቱንና በአገሪቱ ከሚገኝ አንድ ቅርንጫፍ ውጪ ለ6 ሺ 561 ቅርንጫፎች መድረሱን ሰሞኑን አስታውቋል፡፡

ከብር ለውጡ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ብሔራዊ ባንክ ከ74 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ አሮጌውን ብር ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሰብስበዋል፡፡

የባንኩ ምክትል ገዥ አቶ ሰለሞን ደስታ እንደገለጹት፣ በአሁኑ የብር ለውጥ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ጠቁመው፣ ከአንድ ቅርንጫፍ ውጪ በሁሉም የባንክ ቅርንጫፎች አዲሱ የብር ኖት መሠራጨቱን አመልክተዋል፡፡ በአንዱ ቅርንጫፍ አዲሱን የብር ኖት ማድረስ ያልተቻለውም ከፀጥታ ችግር ጋር ስለመሆኑም ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡

በትናንቱ የብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ገለጻ፣ ከአዲሱ የብር ኖት ለውጥ ጋር በተያያዘ አዲስ የተከፈቱ የባንክ አካውንቶች ቁጥርን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ከተሰጠው መረጃ የተለየ አኃዝ የሌለ መሆኑን ነው፡፡

ቀደም ብሎ በዋና ገዥው በተሰጠ መግለጫ በብር ለውጥን ምክንያት ከ580 ሺሕ በላይ አዳዲስ የባንክ ሒሳቦች መከፈታቸው የተገለጸ ቢሆንም፣ ትናንት መግለጫ የሰጡት ምክትል ገዥው የተከፈቱት አዳዲስ የባንክ ሒሳቦች 273 ሺሕ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡   

የአካውንቶቹ ቁጥር ከፍና ዝቅ ሊል ይችላል በሚል የጠቀሱት አቶ ሰለሞን፣ በእነዚህ 273 ሺሕ አዳዲስ የባንክ አካውንቶች እስካሁን ከ13 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡

በኢኮኖሚ ውስጥ ይዘዋወራል ተብሎ ከሚገመተው 140 ቢሊዮን ብር አንፃር አሁን የተሠራጨው አዲሱ የብር ኖት የ90 ቢሊዮን ብር አካባቢ በመሆኑ የገንዘብ ለውጡ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን የሚያመለክት መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

  

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top