Connect with us

ለትግራይ ክልል የመጣው ድሮን የደህንነት ፍተሻ አሟልቶ ባለመገኘቱ ፍቃድ ተከለከለ

ሰው አልባ አውሮኘላን (ድሮን) በዕርዳታ ተገኘ
FBC

ዜና

ለትግራይ ክልል የመጣው ድሮን የደህንነት ፍተሻ አሟልቶ ባለመገኘቱ ፍቃድ ተከለከለ

ለትግራይ ክልል የመጣው ድሮን የደህንነት ፍተሻ አሟልቶ ባለመገኘቱ ፍቃድ ተከለከለ

የሚጠበቅበትን የደህንነት ፍተሻ መስፈርት አሟልቶ እንዳይገባ የተከለከለ ሰው አልባ በራሪ ቁስ (ድሮን) አለመኖሩን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛዉ ገለጹ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ በኤጀንሲው ለጋዜጠኞች ስለ በተቋማዊ ሪፎርም እና ቀጣይ የአምስት ዓመት የትኩረት አቅጣጫ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡

ድሮን ወደ ሃገር ወስጥ ሲገባ የራሱ የሆነ የአሰራር ስርዓት ውያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ በሀገሪቱ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የትግራይ ክልልን ጨምሮ የተለያዩ ክልሎች ድሮኖችን ለማስገባት ጥያቄ አቅርበው በመመሪያው መሰረት እየተስተናገዱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ወደ ትግራይ ክልል ድሮን እንዳይገባ ተደርጓል የተባለው ጉዳይም በመጀመሪያ ደረጃ ድሮኑ ጥናት እና ሪቨርስ ኢንጂነሪነግ  ዓላማ በሚል የመጣ መሆኑን ጠቅሰው በመቀጠልም  ድሮኑ ለጸረ-ዓረም ኬሚካል መርጫ ዓላማ እንደሚውል የተገለፀ ሲሆን ከሰሞኑ ደግሞ ለአንበጣ መንጋ መከላከል ዓለማ በሚል መጠየቁን አንስተዋል፡፡

ኤጀንሲው በድሮኑ ላይ የደህንነት ፍተሻ ባደረገበት ወቅት ድሮኑ የአጠቃቀም እና ተጓዳኝ ጉዳዮች መግለጫ የሌለው ከመሆኑ ባሻገር ከእስራኤል እንደተላከ ቢገለጽም ምርቱ ግን ከቻይና እንደሆነ በዚሁ ወቅት መታወቁን መግለጻቸውን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። 

ሆኖም የድሮኑ ትክክለኛ ዓላማ እና የሚሰጠውን አገልግሎት የደህንነት ተጋላጭነትን የሌለው መሆኑን ማጣራት የኤጀንሲው ሃላፊነት መሆኑን ያወሱት ዋና ዳይሬክተሩ ለአንበጣ መከላከል ተብሎ የተጠየቀው ድሮን የደህንነት ፍተሻ አሟልቶ ባለመገኘቱ ፍቃድ ያልተሰጠው መሆኑን አስረድተዋል፡፡(FBC)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top