Connect with us

ምክር ቤቱ ልዩ ልዩ ሹመቶችን አጸደቀ

ምክር ቤቱ ልዩ ልዩ ሹመቶችን አጸደቀ
Photo: Social Media

ዜና

ምክር ቤቱ ልዩ ልዩ ሹመቶችን አጸደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደው ባለው በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) የቀረቡትን የሚኒስትሮች ሹመት አጽድቋል፡፡
በዚህም መሠረት፡-

1. ዶክተር ቀነዓ ያዴታ የኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር
2. ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
3. ዶክተር ሳሙኤል ሁርቃቶ የኢፌዴሪ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር
4. ኢንጅነር ታከለ ኡማ የኢፌደሪ ማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ሆነው ሹመታቸው በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡

ሚኒስትሮቹ ከዚህ ቀደም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹመቱ ተሰጥቷቻቸው በምክር ቤቱ ማጸደቅ ብቻ የሚቀራቸው እንደነበሩ የሚታወስ ነው፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የ40 የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኞችን ሹመት በአምስት ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ እና የ50 የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኞችን ሹማት ደግሞ በሦስት ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡

ዕጩ ዳኞቹም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ አማካኝነት በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ መፈጸማቸውን ምክር ከምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡

መስከረም 12/2013ዓ.ም (ኢዜአ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top