Connect with us

በ13ኛ ዙር ኮንደምኒየም የደረሳቸው ዕድለኞች ቤታቸውን ሊረከቡ ነው

በ13ኛ ዙር ኮንደምኒየም የደረሳቸው ዕድለኞች ቤታቸውን ሊረከቡ ነው

ዜና

በ13ኛ ዙር ኮንደምኒየም የደረሳቸው ዕድለኞች ቤታቸውን ሊረከቡ ነው

በመዲናዋ በ2011 ዓ.ም የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ወጥቶላቸው ውል ላልገቡ እና ቁልፍ ላልተረከቡ እድለኞች ውል ማስገባትና ቁልፍ ማስረከቡ በአፋጣኝ እንዲፈፀም ማሳሰቢያ ተሰጠ።

በአዲስ አበባ በየካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም በተደረገው ዕጣ ማውጣት ስነ-ስርአት ዕጣ ወጥቶላቸው ውል ላልገቡ እና ቁልፍ ላልተረከቡ ባለ ዕጣዎች ውል ማስገባትና ቁልፍ ማስረከቡ በአፋጣኝ እንዲፈፀም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሳሰበ።

የከተማ አስተዳደሩ በየወቅቱ የሚነሱ የነዋሪዎቹን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ የጋራ መኖርያ ቤቶች ጉዳይ አንዱና የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ የበዛበት ሆኖ ቆይቷል፡፡

በተደረገው ማጣራት እና የስራ ሪፖርት መሰረት ዕጣ ወጥቶላቸው ለባለ ዕጣዎች እጅ ያልደረሱ ቤቶች መኖራቸውን ማወቅ ተችሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ40/60 እና 20/80 ፕሮግራሞች የተገነቡ ቤቶችን የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም ዕጣ ማውጣቱ የተገለፀ ሲሆን ሆኖም ቤቶቹ በቂ የመሠረተ ልማት በሌለባቸው የማስፋፊያ አካባቢዎች በመገንባታቸው እና በሚፈለገው ልክ አጠቃላይ የሳይት ስራው በወቅቱ ባለመጠናቀቁ ለባለ እድለኞች ሳይተላለፉ መቆየታቸውን የከተማው አስተዳደር በመረዳቱ እጣ ወጥቶላቸው ውል ላልገቡ እና ቁልፍ ላልተረከቡ ባለ ዕጣዎች ውል ማስገባትና ቁልፍ ማስረከቡ በአፋጣኝ እንዲፈፀም አሳስበዋል።

በመሆኑም በ20/80 ፕሮግራም የዕጣው አሸናፊ ሆነው ውል ላልፈጸሙ 32 ሺህ 653 ባለ እድለኞች ውል ማዋዋሉ የተጀመረ ሲሆን በቅርቡ ቁልፍ የሚረከቡ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በ40/60 ፕሮግራም ከዚህ ቀደም ውል ለፈጸሙ 18 ሺህ 576 እድለኞች ቁልፍ የማስረከብ ስራ መጀመሩንም የከተማ አስተዳደሩ ጨምሮ አስታውቋል፡፡(FBC)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top