Connect with us

“ከ1 ነጥብ 5 ሚልየን ብር በላይ በቤት ውስጥ ማከማቸት ያስጠይቃል” ዶ/ር ይናገር ደሴ

"ከ1 ነጥብ 5 ሚልየን ብር በላይ በቤት ውስጥ ማከማቸት ያስጠይቃል" ዶ/ር ይናገር ደሴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ
Photo: Ethiopian Reporter

ኢኮኖሚ

“ከ1 ነጥብ 5 ሚልየን ብር በላይ በቤት ውስጥ ማከማቸት ያስጠይቃል” ዶ/ር ይናገር ደሴ

“ከ1 ነጥብ 5 ሚልየን ብር በላይ በቤት ውስጥ ማከማቸት ያስጠይቃል” ዶ/ር ይናገር ደሴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ

“…በእኛ እምነት ይህንን ያህል ጥሬ ገንዘብ በእነዚህ ቦታዎች ላይ መቀመጥ አለበት የሚል እምነት የለንም፡፡ በባንክ ሥርዓት ውስጥ ቢያልፉ ተመራጭነት አላቸው ወይም የባንክ ሥርዓትን የተከተለ የጥሬ ገንዘብ አስተዳደር ቢኖር ይመረጣል፡፡

የጥሬ ገንዘብ በየዕለቱ የሚፈልጉ በርከት ያሉ ድርጅቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ይህንን ታሳቢ በማድረግ እስከ 1.5 ሚሊዮን ብር የሚቀመጠውም ቢሆን ምናልባት በሥራቸው ምክንያት ይህንን ገንዘብ የሚፈልጉ ካልሆኑ በቀር እስከ 1.5 ሚሊዮን ብርም መያዛቸው አይበረታታም፡፡ በባንክ ሥርዓት ውስጥ እንዲስተናገድ ነው የሚፈለገው፡፡

ይህም ሆኖ ግን እስከ 1.5 ሚሊዮን ብር ድረስ ይፈቀዳል፡፡ ከዚያ በላይ የተገኘበት ግን ሕገወጥ ነው፡፡ ለዚህ ተብሎ የተዘጋጀው መመርያ ያስቀጣል ነው የሚለው፡፡

ስለዚህ በዚህ ረገድ አንደኛው ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመቆጣጠር ከባንክ ውጭ ገንዘብ ማስቀመጥን እንዳይበረታታ ለማድረግ ወይም ደግሞ በዚህ ሥራ የተሰማሩ ሰዎች እንደልባቸው መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብ በቤት እያስቀመጡ ችግር እንዳይፈጥሩ ለማድረግ ነው፡፡ አንዳንዴ እዚህም እዚያ ገንዘብ የሚያስቀምጡ ሰዎች ገንዘቡን ለሕገወጥ ተግባር ሊያውሉት ስለሚችሉ ይህንን ለመቆጣጠር የወጣ መመርያ ነው ተብሎ ሊወሰድ ይችላል፡፡

መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብ እዚህም እዚያ ማስቀመጥ ከታክስ ሥወራ ጋር የተያያዘ ወንጀል ሊፈጸምበት ስለሚችል ሕጋዊ አሠራርን ለማስፈን ይህ መመርያ ጠቀሜታ አለው፡፡ በዚህ ሥርዓት ሀብቱና ገንዘቡ የሚታወቅ የንግድ ማኅበረሰብ ለመፍጠር ወደዚህ አሠራር ማስገባት ጠቃሚ ይሆናል፡፡

ሌላው የዚህ መመርያ ጠቀሜታ ተደርጎ የሚወሰደው በቤት ውስጥ ወይም ከባንክ ውጭ የሚቀመጥ ገንዘብ ለብልሽትም የመዳረግ ዕድሉ ሰፊ ስለሆነ ይህንንም አደጋ ይከላከላል፡፡ ስለዚህ እንዲህ ያሉ ጉዳዮች ታሳቢ ተደርጎ ነው ይህ መመርያ የወጣው፡፡…”(ሪፖርተር)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top