Connect with us

የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን የደኅንነት ፍተሻ ማጠናቀቁ ታወቀ

የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን የደኅንነት ፍተሻ ማጠናቀቁን የአውሮፓ የበረራ ደኅንነት ኤጀንሲ አስታወቀ
A Boeing 737 MAX is pictured arriving at Vancouver International Airport on Tuesday to begin test flights. (Ben Nelms/CBC)

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን የደኅንነት ፍተሻ ማጠናቀቁ ታወቀ

የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን የደኅንነት ፍተሻ ማጠናቀቁን የአውሮፓ የበረራ ደኅንነት ኤጀንሲ አስታወቀ።

ከአሰራሩ ጋር በተያያዘ ነው በተባለ ምክንያት ሁለት አደገኛ አደጋዎች ተከስተው በዓለም ዙሪያ በረራ እንዲያቆም የተደረገው የቦይንግ 737 ማክስ የመጀመሪያ የበረራ ሙከራ መጠናቀቁን የኤጀንሲው የአውሮፕላን የበረራ ደኅንነት ባለሥልጣኑ ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡

ባለፈው ሳምንት በአውሮፓ የአቪዬሽን ደኅንነት ኤጄንሲ በካናዳ ቫንኮቨር የሙከራ በረራዎች መከናወናቸውን እና መጠናቀቃቸውን ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡ አውሮፕላኑን ወደ አገልግሎት ለመመለስ በሙከራ በረራዎች ወቅት የተሰበሰቡ መረጃዎች በመተንተን ላይ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

ከዚያም በሚቀጥለው ሳምንት በለንደን ግምገማውን ለመጀመር በታቀደው መሰረት ለአውሮፓ የአቪዬሽን ደኅንነት ኤጀንሲ የጋራ ኦፕሬሽን ምዘና ቦርድ ይተላለፋል ተብሏል።

የአውሮፓ የአቪዬሽን ደኅንነት ኤጀንሲ የራሱን ዳግም የማረጋገጫ ፈተና ሰኔ ላይ እንደጀመረና ቦይንግ 737 ማክስን ዳግም ወደ አገልግሎት ለመመለስ ከአሜሪካ የፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር ጋር እየሰራ መሆኑ ታውቋል። ነገር ግን ደኅንነቱ ከተረጋገጠ በኋላ ብቻ ወደ በረራ እንደሚመለስ አስታውቋል፡፡

አየር መንገዶች ማክስን 737 አውሮፕላንን መጠቀም የጀመሩት (እ.ኤ.አ.) በ2017 ነበር፤ (እ.ኤ.አ.) በ2018 በኢንዶኔዥያ እና (እ.ኤ.አ.) በ2019 በኢትዮጵያ አደጋዎች ደርሰው በረራ እንዲያቆሙ ከመደረጉ በፊት ወደ 4 መቶ የሚጠጉ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በአገልግሎት ላይ ነበሩ፡፡

የአደጋው ምክንያት መርማሪዎች (MCAS) የተባለው የበረራ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌር በተሳሳተ ንባብ ላይ በመመርኮዝ የአውሮፕላኖቹን አፍንጫ ወደ ታች እንዲዘቀዘቅ እንዳደረገው ጠቁመዋል፡፡ ባለፈው ወር የበረራ ፈቃድ እገዳው ከመነሳቱ በፊት የፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር የሚያስፈልጉትን የዲዛይን ለውጦች ዝርዝር አሳይቷል ተብሏል፡፡

ምንጭ፡-አሶሼትድ ፕረስ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top