Connect with us

“በተቃራኒ አቅጣጫ የሚጓተቱ ፍላጎቶቻችን በመግራት፣ ለሀገር ያለንን ፍቅር …

“በተቃራኒ አቅጣጫ የሚጓተቱ ፍላጎቶቻችን በመግራት፣ ለሀገር ያለንን ፍቅር እናሳይ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ
Photo: EPA

ዜና

“በተቃራኒ አቅጣጫ የሚጓተቱ ፍላጎቶቻችን በመግራት፣ ለሀገር ያለንን ፍቅር …

“በተቃራኒ አቅጣጫ የሚጓተቱ ፍላጎቶቻችን በመግራት፣ ለሀገር ያለንን ፍቅር እናሳይ” ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

የጠነከረች ኢትዮጵያን ለመገንባት ለሚደረገው የብልጽግና ጉዞ በተቃራኒ አቅጣጫ የሚጓተቱ ፍላጎቶቻችንን በመግራት፣ ለሀገር ያለንን ፍቅር እናሳይ፤ አዎንታዊ ሚናም እንጫወት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

የጋራ ግብ ከያዝን የሀገራችን ህልውና ጠብቀን የጋራ ድል እንደምንቀዳጅ ምንም ጥርጥር የለውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁለት ተቃራኒ ዋልታዎች ላይ የሚንጠለጠሉ ፍላጎቶቻች ማቀራረብ መቻል አለባቸው ብለዋል።

አንድ ርምጃ ወደ መሐል ለመቅረብ የማይፈቅድ እንኳን አንድ ሀገርን ቀርቶ አንድ ቤተሰብን እንደማይገነባ የገለጹት ዶ/ር አብይ እኔ ያልኩት ካልሆነ በሚል ግትርነት የምናደርገው ጉዞ፥ ሀብት፣ ጊዜና ጉልበት ከማባከን ውጭ ማንንም ምንም የማይጠቅም ነው ብለዋል።

ስለዚህም በተቃራኒ አቅጣጫ የሚጓተቱ ፍላጎቶቻችን በመግራት ለሀገር ያለንን ፍቅር እናሳይ፤ የጠነከረች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው የብልጽግና ጉዞ አዎንታዊ ሚናችንን እንወጣ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።(ኢኘድ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top