Connect with us

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለሙያዎች የአውሮፕላን ክንፍ ላይ የምህንድስና ማሻሻያ አደረጉ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጥገና ባለሙያዎች የአውሮፕላን ክንፍ ላይ የምህንድስና ማሻሻያ አደረጉ
Photo: Social Media

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለሙያዎች የአውሮፕላን ክንፍ ላይ የምህንድስና ማሻሻያ አደረጉ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ጥገና ባለሙያዎች በአፍሪካ አቪየሽን ታሪክ የመጀመሪያ ሊባል የሚችል የአውሮፕላን ክንፍ ላይ የምህንድስና ማሻሻያ /winglet modification/ አደረጉ።

ማሻሻያው የተደረገው አየር መንገዱ በሚያበራቸው የቦይንግ 767 አውሮፕላኖች ላይ ሲሆን፣ ይህም በአመት እስከ 500 ሺህ ጋሎን ነዳጅ እንዲቆጥብ ያስችለዋል ተብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ ማሻሻያው 277 ሺህ ሜትሪክ ቶን የካርበን ልቀትንም የሚያስቀር በመሆመኑ አየር መንገዱ በአካባቢ ጥበቃ የሚያደርገውን ጥረት የሚያግዝ ነው።

69 የሚሆኑ የአየር መንገዱ የአውሮፕላን አካል ጥገና ባለሙያዎች ሌት ተቀን እና በእረፍት ቀናቸውም በመስራት ጭምር ፕሮጀክቱን በስኬት ማጠናቀቃቸው ተገልጿል። #ET

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top