Connect with us

ዓለማቀፉ ጣናን መልሶ ማቋቋም ማኅበር የእንቦጭ ማስወገጃ ማሽን በስጦታ አስረከበ

ዓለማቀፉ ጣናን መልሶ ማቋቋም ማኅበር የእንቦጭ ማስወገጃ ማሽን በስጦታ አስረከበ
Photo: Social Media

ዜና

ዓለማቀፉ ጣናን መልሶ ማቋቋም ማኅበር የእንቦጭ ማስወገጃ ማሽን በስጦታ አስረከበ

ከፍተኛ መጠን አረም የማጨድ አቅም ያለው የእንቦጭ ማጨጃ ማሽን ለአማራ ክልል መንግስት በስጦታ መስጠቱን ዓለማቀፉ ጣናን መልሶ ማቋቋም ማኅበር አስታወቀ።

ተቀማጭነቱ በአሜሪካ የሆነው ዓለማቀፉ ጣናን መልሶ ማቋቋም ማኅበር በአሜሪካና በእንግሊዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያዎያንን በማስተባበር እንዲሁም ዋሺንግተን ዲሲ ከሚገኘው ደብረገነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ባገኘው ድጋፍ የገዛውን የእንቦጭ ማጨጃ ማሽን ዛሬ ለክልሉ መንግስት በስጦታ አበርክቷል።

ማሽኑ በ5 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር እንደተገዛ ማኅበሩ ለአብመድ በላከው መረጃ አመላክቷል፤ በአንድ ጊዜ 28 ሜትር ኪዩብ አረም ማረምና መሸከም የሚችል መሆኑንም አስታውቋል።

ዓለማቀፉ ጣናን መልሶ ማቋቋም ማኅበር ከዚህ ቀደም የተለያዩ ድጋፎች ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሷል። በ2010 ዓ.ም የእንቦጭ ማጨጃ ማሽን በስጦታ መስጠቱንም በአብነት ጠቅሷል። የተለያዩ የስልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱም ተመላክቷል።

ማኅበሩ ባለፈው ዓመት ከክልሉ የዱር እንስሳት ልማትና አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተውጣጡ ባለሙያዎችን ወደ ዩጋንዳ ወስዶ በእንቦጭ አወጋገድ ስልቶች ዙርያ ስልጠናና ልምድ እንዲቀስሙ ማድረጉንም አስታውሷል።

ጣናን ከተደቀነበት አደጋ ለመታደግ የሚያበረክተውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም የማኅበሩ ዋና ሰብሳቢ ሰሎሞን ክብረት (ዶክተር) አስታውቀዋል። ሌላ የእንቦጭ ማጨጃ ማሽን በካናዳ አሰርቶ የጨረሰ መሆኑንም ገልጸዋል።

የክልሉ መንግስት የሚረከባቸውን የእንቦጭ ማጨጃ ማሽኖች በአግባቡ ተጠቅሞ ጣና ሀይቅን የወረረውን የእንቦጭን ሽፋን ለመቀነስ በትኩረት እንዲሠራም አሳስበዋል። #አብመድ

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top