Connect with us

ፓስፖርት ለማግኘት እስከ ስድስት ሳምንት ይፈጃል

ፓስፖርት ለማግኘት እስከ ስድስት ሳምንት ይፈጃል
Photo: Social Media

ዜና

ፓስፖርት ለማግኘት እስከ ስድስት ሳምንት ይፈጃል

ከ700 ሺ በላይ የፓስፖርት ደብተር በክምችት እንደያዘ የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል በቂ ፓስፖት መግባቱን ገልፀው በፓስፖርት ማግኘት ሂደት ውስጥ የሚኖረውን የተንዛዛ ስራ ለመቅረፍ በተለያየ መልኩ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የፓስፖርት እድሳት በተቋሙ መምጣት ሳያስፈልግ በአማራጭነት ኦንላይን ሂደቱን ማከናወን የሚያስችል ስራ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ተደራሽነትን ማስፋት ሌላው አካሄድ ነው፡፡ ሆሳእና፣ ጋምቤላ እና አሶሳ ቅርንጫፍ የመክፈት ሂደቱ እየተጠናቀቀ ነው ያሉት አቶ ሙጂብ በአዲስ አበባም 2 ቅርንጫፍ ከመክፈት የቢሮ ኪራይ ጨረታ አውጥተናል ብለዋል፡፡

እጥረት ሲፈጠር ብልሹ አሰራር ይታያል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በህገወጥ ተዋናዮች ላይ እርምጃ እንደተወሰደ ጠቅሰዋል፡፡

የፓስፖርት እጥረት ባለፉት ሁለት አመታት ግድም በመታየቱ የፓስፖርት መስጫ ግዜ ወደ 75 ቀን ግድም ሆኖ ነበር፡፡ ሆኖም እጥረቱ በመቀረፉ የመስጫ ግዜ ወደ 30 ቀን ወርዷል ብለዋል፡፡ ይህም የተለመደ አሰራር ነው ለምሳሌ በፓስፖርት ምርት ታዋቂ የሆነችው ጀርመን ፓስፖርት ለመስጠት ከ4 እስከ 6 ሳምንት ያስፈልጋል፣ በማለት አብራርተዋል፡፡

አጣዳፊ ጉዳይ ኖሮት ማስረጃ የሚያቀርብ ባለጉዳይ በተጨማሪ ክፍያ በቀናት ፓስፖርቱን ማግኘት እንደሚቻል ታውቋል፡፡(ካፒታል)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top