Connect with us

ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ እንደገና ተወያዩ

ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ እንደገና ተወያዩ
Photo: AP

ዜና

ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ እንደገና ተወያዩ

በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት የተሳተፉበት ውይይት መካሄዱን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሽ በቀለ ተናገሩ።

ሚኒስትሩ በውይይቱ በተወሰኑ ነጥቦች ላይ መግባባት ላይ መደረሱንም አስረድተዋል።

ከዚህ ባለፈ ግን በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ በኢትዮጵያ ዘላቂ ጥቅም ላይ ተፅዕኖ የሚኖራቸው ነጥቦች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ በማስፈለጉ ልዩነት እንደነበርም አንስተዋል።

የግድቡ አሞላልም የግድቡን ተፈጥሯዊ የግንባታ ሂደት በጠበቀ መልኩ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም አሁን ላይ ግድቡን በተመለከተ በሳተላይት የሚታዩ ምስሎች ትክክለኛ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በውይይቱ ላይ ከኬንያ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ማሊ፣ ማዳጋስካር እና ደቡብ አፍሪካ የተውጣጡ 11 ባለሙያዎች ተሳትፈዋልም ነው ያሉት።(ኤፍ ቢ ሲ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top