Connect with us

“ኮምፒውተር ላይ ዓይን ተክሎ መዋል የአንገት ዲስክ ይጎዳል”

"ኮምፒውተር ላይ ዓይን ተክሎ መዋል የአንገት ዲስክ ይጎዳል"
Photo: Social Media

ጤና

“ኮምፒውተር ላይ ዓይን ተክሎ መዋል የአንገት ዲስክ ይጎዳል”

“ኮምፒውተር ላይ ዓይን ተክሎ መዋል የአንገት ዲስክ ይጎዳል”

ዶክተር ብሩክ ላምቢሶ፣ የአጥንት ቀዶ ሕክምና ኮንሰልታንት

ስለዲስክ መንሸራተት

የዲስክ መንሸራተት ብዙ ምክንያቶች አሉት፡፡ የመንሸራተቱ ዋንኛው መንስዔ ግን ከአኗኗር ባህሪ ለውጥ የተነሳ ነው፡፡ ብዙ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ አጭሯንም፣ ትንሻንም መንገድ በተሽከርካሪ መሄድን መምረጥና ረጅም መንገድ በእግር አለመሄድ ሌላው መንስዔዎች ሲሆን ከኑሮ ወጣ ውረድ የተነሳ ይመሻል፣ ይነጋል፣ ሁሌ ወደ ሥራ ሩጫ ነው፡፡ ማረፊያ ጊዜ የለም፡፡

በዚህም የተነሳ ብዙ ይቆማል፣ ወይም ቁጭ ይባላል፡፡ ይህ ሁሉ ለዲስክ መንሸራተት መንስዔ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ኮምፒውተር ላይ ዓይን ተክሎ መዋል የአንገት ዲስክን ይጎዳል፡፡ በመቆም ደግሞ የወገብ ዲስክ ይታወካል፡፡ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች አለመኖር ደግሞ ለበሽታው መስፋፋት መንስዔ ሆኗል፡፡

የዲስክ መንሸራተት ዱሮ የ19 እና የ20 ዓመት ዕድሜ ባላቸው ታዳጊ ሕጻናት ላይ አይተን አናውቅም ነበር፡፡ አሁን ግን እያየን ነው፡፡ ሕጻናት የስፖርት እንቅስቃሴ አያደርጉም፣ ላድርግ ቢሉም ቦታ የለም፡፡ የልጆች መጫወቻ ቦታ ማጣት ለዲስክ መንሸራተት መንስኤ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ለስኳር ሕመም በሽታና ለውፍረት ዳርጓቸዋል፡፡

እንደው በአጠቃላይ በሰለጠነው ዓለም ከከተሜነት ጋር ተይይዘው የሚመጡና የምናያቸው በሽታዎች በአሁኑ ጊዜ በአገራችንም መጥተዋል፡፡ ዱሮ አንድ ሕጻን ላይ የስኳር በሽታ መኖር እንደ ጉድ ነበር የሚታየው፡፡ አሁን ግን የሕጻናት ስኳር በሽታ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ተለምዷል፡፡ እየበዛም መጥቷል፡፡ በአገራችን ከሶስት ሚሊዮን የሚጠጉ የስኳር ሕሙማን ይገኛሉ፡፡

በአገራችን አሁን ያለው የአንድ ሰው በሕይወት የመቆየት ዕድሜ ጣሪያ 64 ዓመት ነው፡፡ ብዙ በኖርን ቁጥር በዛው መጠን ዲስኮችና መገጣጠሚያዎቻችን ሁሉ ያረጃሉ፡፡ ከአንገታችን እስከ “ጭራችን” ድረስ 33 ዲስኮች እንዳሉ መታወቅ ይኖርበታል፡፡

ዕድሜያቸው 60፣ 70 እና ከዛም በላይ የሆኑ ሰዎች ዲስክና መገጣጠሚያዎች ብዙ በመሥራታቸውና በማርጀታቸው መተካካት ያስፈልጋቸዋል፡፡ መተካትም የሚችሉ መለዋወጫዎች በአገራችን አሉ፡፡ እንደ ከዚህ በፊቱ ሕንድ፣ ታይዋን ወዘተ መሄድ አያስፈልግም፡፡ ያፈነገጠውን ዲስክ እናወጣውና አጠገቡ ያሉትን ሁለት አጥንቶች እናጋጥማቸዋለን፡፡ እነዚህን ሰርጀሪዎች ለመሥራት ብዙም አስቸጋሪ አይደለም፡፡ (ታደሰ ገብረማርያም – ሪፖርተር)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top