Connect with us

ዶ/ር ደብረፅዮን የህዳሴን ግድብ በማዳከም ተከሰሱ

ዶ/ር ደብረፅዮን የህዳሴን ግድብ በማዳከም ተከሰሱ
Photo: Social Media

ኢኮኖሚ

ዶ/ር ደብረፅዮን የህዳሴን ግድብ በማዳከም ተከሰሱ

“የህዳሴ ግድብ ግንባታ በወቅቱ ቦርድ ሰብሳቢ በነበሩት ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል አድራጊ ፈጣሪነት በፍጥነት ተዳክሞ ለከፍተኛ ኪሳራ ተዳርጓል”አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ

የቀድሞ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር በአሁኑ ወቅት በሩሲያ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ በ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት ፣ የህዳሴ ግድቡ አቶ መለስ በህይወት እስከነበሩበት ጊዜ ድረስ በየወሩ ይገመገም የነበረ ሲሆን ከእርሳቸው ህልፈት በኋላ በየወሩ መገምገሙ ቀርቷል፡፡

የወቅቱ የቦርድ ሰብሳቢ በክላስተር አደረጃጀት በሁለት ወር አንድ ጊዜ እንዲታይ ብለው አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን አስታውሰው ፣ ሰብሳቢው አሠራሩን ተግባራዊ ሳይደርጉ መቅረታቸውንም አመልክተዋል። በዚህ ሁኔታ የህዳሴ ግድቡን ፕሮጀክት የመብራት ኃይል ቦርድ አካልም ይገመግመው እንዳልነበር ጠቁመዋል::

ፕሮጀክቱን በሚመለከት በየጊዜው ለቦርዱ ጥያቄ እናቀርብ ነበር ያሉት አምባሳደር አለማየሁ፣ ቦርዱም ገምግሞ ወደ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የግምገማውን ውጤት አይልክም ነበር ብለዋል፡፡
የዘርፉ ባለቤት ብንሆንም ተገልለን ነበር፤ ሪፖርትም ከመብራት ኃይል እየወሰድን ጉድለቶቹን እንናገር ነበር ሲሉም ተናግረዋል::

እንደ አምባሳደሩ ገለጻ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከመብራት ኃይል የሚያገኘውን መረጃ ይዞ እንደ ዘርፍ መግለጫ በሚሰጡበት ወቅት እንኳን ‹‹ምን አግብቷችሁ ነው መግለጫ የምትሰጡት›› በማለት በቦርድ ሰብሳቢው በኩል ቁጣ ይደርስባቸው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በዚህ ሁኔታም ፕሮጀክቱ ከህዝብ ፕሮጀክትነቱ ወርዶ የአንድ ግለሰብ ፕሮጀክት ሆኖ እንደነበር አመልክተዋል። ይህም የግድቡን ግንባታ ለውድቀት ከመዳረጉ ባለፈ ‹‹በአገራችን ታሪክ የሚያሳዝን ድርጊት ሆኖ አልፏል›› ብለዋል፡፡

በወቅቱ የህዳሴ ግድቡ ሥራና ውሳኔዎች በሰብሳቢው
ውሳኔ ስር የነበሩ መሆናቸው ትክክል እንዳልሆነ ለቦርድ አባላት ቢነገርም የቦርድ አባላትም ፕሮጀክቱን እንደማይገመግሙ ማስታወቃቸውን አመልክተው፤ ግንባታው በአካል ባለመገምገሙ ብቻ ትልቅ ውድቀት
እንደነበር ገልጸዋል።

በወቅቱ የነበረውን ቦርድ ችግሮች በሚገባ ለማየት አሁን የተቀየረው ቦርድ በአጭር ጊዜ ያመጣውን ለውጥ ማየት አሳማኝና በቂ ነው ብለዋል።

(ምንጭ:- አዲስ ዘመን ጋዜጣ)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top