Connect with us

አካባቢያችንን መከራ ውስጥ ከትተን የምናከብረው የዓለም አካባቢ ቀን

አካባቢያችንን መከራ ውስጥ ከትተን የምናከብረው የዓለም አካባቢ ቀን
Prime Minister Abiy Ahmed visited Lake Tana along with other high lever officials including DPM Demeke Mekonnen, and Amhara region president Gedu Andargachew

ኢኮኖሚ

አካባቢያችንን መከራ ውስጥ ከትተን የምናከብረው የዓለም አካባቢ ቀን

አካባቢያችንን መከራ ውስጥ ከትተን የምናከብረው የዓለም አካባቢ ቀን፡፡
******
ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ዛሬ በመላው ዓለም የሚከበረውንና ኢትዮጵያም የምታከብረውን የዓለም አካባቢ ቀን አካባቢያችንን መከራ ውስጥ ከትተን የምናከብረው በዓል ነው ይለናል በተከታዮ ዘገባው፡፡)
ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

ለትውልድ መጨነቁን ትተነዋል፡፡ ለራሳችን እንኳን ማሰብ አቅቶን አሁን የሚባለውን ሰዓት እያጨለምነው ነው፡፡ ዛሬ የዓለም አካባቢ ቀን ነው፡፡ ዓለም ብዝኃ-ሕይወት ብሎ ለ47ኛ ጊዜ ያከብረዋል፡፡ ኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ለዘላቂ የብዝኃ-ሕይወት ልማት በሚል መሪ ቃል ለ27ኛ ጊዜ ቀኑን ታከብራለች፡፡

ኮሎምቢያ የምታስተናግደው ዓለም አቀፋዊ የዚህ ዓመት ኩነት ከአካባቢው መታረቅ ባቀተው የሰው ልጅ መዘዘኛ ጠባይ በተከሰተ ችግር ምክንያት ደብዝዟል፡፡ ኢትዮጵያም በዓሉን ስታከብር ከአካባቢዋ ጋር ሳትታረቅ ነው፡፡ አከባቢን የመጠበቅ ጉዳይ ዛሬው ዋና አጀንዳ አይደለም፡፡

ይህንን በዓል ስናከብር በዋዜማው እንኳን ስምንት የአፍሪካ ዝኆኖች ከማጎ ደን ውስጥ ከአፈር ቀላቅለን ነው፡፡ ከዚህ በላይ ከአካባቢ መኳረፍ የለም፡፡ በዚህ ዓመት ምን ያህል የተፋሰስ ስራ ሰራን? ስንት ሄክታር አፈር ተከተረ? ስንት ዛፍ ከጥፋት ታደግን?

ኢትዮጵያ ድህነቷ ከተፈጥሮ መቀያየሟ ነው፡፡ መሬቷ ነጥፏል፡፡ ዛሬም በዜማ እንጂ ለምነቱ በተግባር አፈሯን በክብር የምትሸኝ ሀገር ሆናለች፡፡

ይኼንን በዓል ስናከብር በዕለቱ ጣር ላይ ስላለ ሐይቃችን በቃ ብለን በጋራ ሳንነሳ ነው፡፡ ጣና በገባበት መከራ ውስጥ ሆኖ ስንት የዓለም አካባቢ ቀን አከበርን? በዓለም አካባቢ ቀን ቆጠራችን አብጃታ ከታመመ ስንት ጊዜ ኾነው? የስምጥ ሸለቆ ሐይቆች ጤናስ እንዴት ነው? ጉልበተኛ የወረረው የቤጃሚዝ ፓርክ ህልውናስ ከአባይ ተፋሰስ ጋር ያለው ዝምድና? የባኩሳ ብሔራዊ ፓርክ እርሻ ሆኖ መቅረትስ?

አካባቢ ለአንድ ተቋም የሚሰጥ ነገር አይደለም፡፡ አካባቢ ጥበቃ የመኖር ያለመኖር ጉዳይ ነው፡፡ በተፈጥሮ ቀመር ኢትዮጵያ የአባቶቻችን ሀገር አይደለችም፤ የልጆቻችን ናት፡፡ እነሱ የልጆቻችን ሀገር ናት ስላሉ እኛ ጋር ደርሳለች፡፡ እኛ ግን የጠላቶቻችን ሀገር አድርገን ቆጥረናታል፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር የአካባቢ ችግር አለብን፡፡ ከአካባቢ ተኳርፈን እስከ መቼ እንኖራለን? የሚለው ምላሽ ይሻል፡፡

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top