Connect with us

የአምነስቲ መግለጫ የኦሮሚያ እና የአማራ ክልል መንግስታት አጣጣሉት

የአምነስቲ መግለጫ የኦሮሚያ እና የአማራ ክልል መንግስታት አጣጣሉት
Ethiopia’s Prime Minister Abiy Ahmed. REUTERS/Tiksa Negeri

ዜና

የአምነስቲ መግለጫ የኦሮሚያ እና የአማራ ክልል መንግስታት አጣጣሉት

አምኒስቲ ኢንተርናሽናል የሰብአዊ መብት ጥሰት አለ በሚል ያወጣውሪፖርት የአንድ ወገን አስተያየት የያዘና እውነታውን የሚያሳይ ባለመሆኑ እንደማይቀበሉት የኦሮምያ እና የአማራ ክልል መንግስታት አስታወቁ።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወጣው ሪፓርት በሂደቱ የተሳተፉት መረጃ ሰጭዎች የኦነግ ሸኔ አባላት በመሆናቸው፣ መረጃው በኦነግ ሸኔ አባላት የተፈፀሙ ጥሰቶችን ያላካተቱ በመሆናቸው በጉዳዩ የመንግስትን ሃሳብ ያላካተተ በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው ነው ብሏል ቢሮው በመግለጫው።

በተያያዘም የኦሮምያ ክልል ህግ የማስከበር ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል እና የሚጠሩ ሰላማዊ ሰልፎች ተቀባይነት የላቸውም ብሏል።

የክልሉ የሰላምና ደህንነት ቢሮ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ለውጡ ከግብ እንዳይደርስ ፣ ልማት እንዲደናቀፍና ፣ ህዝቡ ሰላም እንዲያጣ የሚሰሩ አካላት መኖራቸውን ገልጿል።

የቢሮው ሃላፊ ጅብሪል መሀመድ እንዳሉት ይሄው ሃይል በአንድ በኩል ትጥቅ በሌላ በኩል ህጋዊ አካሄድን እየተከተለ፣ ሀገር እንድትሸበር እና ህዝቡ በመንግስት እምነት እንዲያጣ ሀሰተኛ መረጃን በማሰራጨት ላይ ይገኛል።

ለበርካታ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ንፁሃን ዜጎች ሞት ምክንያት ሆኖ ሳለ፣ መንግስት የፈፀመው በማስመሰል መገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም የሃሰት ወሬ እያሰራጨ መሆኑም በመግለጫው ተገልጿል።

መገናኛ ብዙሃኑም ለሽብር የሚያነሳሱ ፣ ሰላምን ለማወክ እየተንቀሳቀሱ፣ በመሆኑ በህግ እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል ብለዋል።
አሁንም ለውጡን የማይፈልጉ አባላት ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተቃረነ መልኩ በሃሰተኛ መረጃና ድብቅ አጀንዳ ባላቸው አካላት ሰልፍ እየተጠራ መሆኑም ተደርሶበታል።

የዚህ ሰልፍ መነሻዎችም፣ የመንግስትን ስልጣን ለመያዝ ወይንም ለመጋራት፣ የሽግግር መንግስት የማቋቋም ፍላጎት፣ በለውጡ ስልጣናቸውን ያጡ ጥግ የያዙ የህውሓት ባለስልጣናት እጅ ናቸው ብለዋል።

ሰልፉም ሀገሪቷ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ መሆኗ፣ የህዳሴ ግድቡ ጉዳይ ከመቼውም ጊዜ በላይ በግብፅ ፍላጎት በባንዳዎች ሴራ አደጋ ላይ በመውደቁ፣ ከስልጣናቸው የተገፉ የቀድሞ ባለስልጣናት ብጥብጥ በመፍጠር እንደገና የመመለስ ፍላጎት ያላቸው እና የክልሉ መንግስት ያዳከመው የሽምቅ ተዋጊ እንደገና ለማንሰራርት ሁከት የመፈጠር ፍላጎት ያለው በመሆኑ፣ በምንም መልኩ መካሄድ የማይችል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ነው የተባለው፡፡

ህዝቡም እንደትላንቱ ሁሉ ለውጡን እንዲጠብቅ፣ የፀጥታ መዋቅሩም ህግ የማስከበር ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

በተያያዘ ዜና አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወጣው መግለጫ የተዛባና ሚዛናዊነት የጎደለው መሆኑን የአማራ ክልል ገለፀ።

የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙልነህ ጉዳዩን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫውም አምነስቲ ኢንተርናሽናል በአማራ ክልል በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች በነበረው ችግር ላይ ያቀረበው ሪፖርት ከግጭቱ መነሻ ምክንያት ጀምሮ በርካታ ክፍተቶች ያሉት፣ የተዛባና በአንድ ወገን መረጃዎች ላይ የተመሠረተ ሚዛናዊነት የጎደለው መሆኑን ነው ዳይሬክተሩ የገለፁት።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ግጭት ተፈፀመባቸው በተባሉ ቦታዎች የአማራ ተፈናቃዮች፣ መሠረታዊ የሆኑ የክልሉ መንግስት አመራሮች እና ተቋመት ተጠይቀው ተገቢ መረጃ ተሰብስቦ ሳይካተት ሚዛናዊነት በጎደለው ሁኔታ መግለጫ መስጠቱ መታረም እንዳለበት ተናግረዋል።

ሪፖርቱ በቅማንት ላይ የብሄር ጥቃት እንደተፈፀመ እና ቅማንት ብቻ የጠፈናቀለ አድርጎ ማቅረቡ ሁለቱን ህዝቦች እንደገና ወደቁርሾ የሚመራ፣ ለአንድ ወገን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደተፈፀመ የሚገልፅ ትክክለኛነት የጎደለው ነው ብለዋል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የክልሉ መንግስት እና የፌደራል መንግት የሠሩትን ስራ እውቅና በመንፈግ አንድ ወገንን ማዕከል አድርጎ ሪፖርቱን ማዘጋጀቱ ለሪፖርቱ ሚዛናዊ አለመሆን ማሳይ አድርገው አቅርበዋል አቶ ግዛቸው።

በመሆኑም ድርጅቱ ያወጣውን መግለጫ እንደገና እንዲመለከተው ጠይቋል።(ፋና)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top