Connect with us

በማጎ ብሔራዊ ፓርክ የተገደሉት ዝሆኖች ቁጥር አምስት ደረሰ

በማጎ ብሔራዊ ፓርክ የተገደሉት ዝሆኖች ቁጥር አምስት ደረሰ
Photo Facebook

ዜና

በማጎ ብሔራዊ ፓርክ የተገደሉት ዝሆኖች ቁጥር አምስት ደረሰ

በዛሬው እለት በማጎ ብሔራዊ ፓርኮ ውስጥ በህገ-ወጥ ታጣቂዎች በዝሆኖች ላይ ባደረሱት ጥቃት አራቱ ቀድመው የሞቱ ሲሆን ጉዳት ደርሶበት ነበረ አንድ ዝሆንም መሞቱ ተገልጧል፡፡ ይህም የሞቱት ዝሆኖችን ቁጥር አምስት አድርሶታል፡፡

በዝሆኖች ላይ የደረሰው የታሰበበት ግድያ ትናንት ምሽቱን ጀምሮ እንደነበር የነገሩን የፓርኩ ዋርደን አቶ ጋናቡል ቡልሚ በዝሆኖች ላይ ጥቃቱን ባደረሱት ሁለት ግለሰቦች ላይ ዝሆኖቹ ጉዳት ማድረሳቸው ገልጸውልናል፡፡

ችግሩ የተከሰተው በፓርኩ የሀመር ወረዳ አዋሳኝ አካባቢ ሲሆን በዝሆኖቹ የመልስ ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች የመንግስት አመራሮች መሆናቸውን የገለጡልን የፓርኩ ኃላፊ ግለሰቦቹ እጃቸው ሊኖርበት እንደሚችል ጥርጣሬውን ገልጧል፡፡

ጉዳዩን ለደቡብ ኦሞ ዞን እና ለሚመለከታቸው የክልል ቢሮዎች የደረሰ ሲሆን በሁሉም አካላት ርብርብ ድርጊቱን የፈጸሙት ወንጀለኞች ለህግ እንዲቀርቡ የማድረግ ጥረት ላይ የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ፓርኩ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

የማጎ ብሔራዊ ፓርክ በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል ደቡብ ኦሞ ውስጥ የሚገኝ የዝሆን መዳረሻ ሲሆን የዱር እንስሳቱ በከፍተኛ የጸጥታ ችግር ጉዳት ሲደርስባቸው የቆዩ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ምንጭ:- አረንጓዴ ሐሳቦች

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top