Connect with us

53 የሸገር ዳቦ ማከፋፈያ አውቶብሶች ለ265 ሥራ አጥ ወጣቶች ተሰጡ

53 የሸገር ዳቦ ማከፋፈያ አውቶብሶች ለ265 ሥራ አጥ ወጣቶች ተሰጡ

ኢኮኖሚ

53 የሸገር ዳቦ ማከፋፈያ አውቶብሶች ለ265 ሥራ አጥ ወጣቶች ተሰጡ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለረጅም ጊዜያት አገልግሎት ሳይሰጡ የተቀመጡ ያገለገሉ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችን የዲዛይን ለውጥ ተደርጎላቸው ለከተማው ስራ አጥ ወጣቶች የዳቦ ችርቻሮ ማካፋፈያና የሽያጭ አገልግሎት እንዲሰጡ ውሳኔ ወስኖ በየክ/ከተማው ላሉ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ሀላፊነት መስጠቱን ይታወሳል፡፡

የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅም ከከተማው አስተዳደር የተረከበቸው 53 ያገለገሉ የአንበሳ አውቶቡሶችን ለሸገር ዳቦ ማከፋፈያ ሱቅ በሚያመች መልኩ አስፈላጊውን የዲዛይን ማሻሸያና ጥገና በማድረግ የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢ/ር እንዳወቅ አብጤ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አስራት ንጉሴና ሌሎች የክተማውና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች በተገኙበት አጠነቅቆ በትላንትናው ዕለት አስረከበ፡፡

በርክክብ ስነ -ስርዓቱ ላይ የተገኙ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በም/ከንቲባ ማዕረግ የመንግስትየአገልግሎት ሰጭ ተቋማት አስተባባሪ ኢ/ር እንዳወቅ አብጤ እና የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስ/ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አስራት ንጉሴ ባደረጉት ንግግር የኮሌጁ አመራሮችና ባለሙያዎች ለክ/ከተማው አስተዳደር የተመደቡት 53 አውቶቡሶችን በወጣላቸው የዳቦ ማከፋፈያ የሱቅ ዲዛይን መሰረት አስፈላጊ የውስጥ ዲዛይን ለውጥና ጥገና በማድረግ በወቅቱ አጠናቀው ለአስተዳደሩ በማስረከብ ለታለማላቸው ዓላማ እንዲውሉ ላደረጉት ከፍተኛ ርብርብ አመስግነው ፕሮጀክቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለሙያዎችና የስራ ሀላፊዎች የእውቅና ሰርተፍኬትና ዋንጫ በማበርከት በስራ መስኩ ለሚሰማሩ የወጣቶች ተወካዮች የባሶቹ ቁልፍ አስረክቧል፡፡

ሀላፊዎቹ አያይዘውም የከተማው አስተዳደር ህብረተሰቡን ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመታደግ በሁሉም የአስተዳደሩ መዋቅሮች ከሚሰራቸው የቅድመ መከላከል ስራዎች ጎን ለጎን የስራ አጥ ዜጎችና የአጠቃላይ ማህበረሰቡ የልማት ጥያቄዎችን ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ከመቼውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑ ተናግረው በቀጣይ በሚሰሩ ስራዎችም የኮሌጁ ሙያዊ ድጋፍ ይበልጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ጠይቀዋል፡፡

የክፍለ ከተማው የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ል/ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ከበደ ድሪባ በበኩላቸው የዳቦ መሸጫ አውቶቡሶቹ ለታለማለቸው ዓላማ እንዲውሉ በየወረዳውና በየቀጠናው የሚቀመጡባቸውን ቦታዎች የመለየትና በዚህ የስራ መስክ የሚሰማሩ ስራ አጥ ወጣቶች የማደራጀትና የማስልጠን ስራዎችን መሰራታቸውን ጠቁመው በየደረጃው በሚገኙ የአመራሮችና በባለድርሻ አካላት በስራ መስኩ ለሚሰማሩ ወጣቶች አስፈላጊውን የፈይናንስ እንዲሁም የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እና ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ጭምር ገልፀዋል፡፡

የስራ መስኩ ለ265 የክፍለ ከተማው ስራ አጥ ወጣቶችን ተጠቃሚ ከማድረጉም ባሻገር በአካባቢው ለሚስተዋለው የዳቦ ዋጋ ንረትና የአቅርቦት እጥረት ችግሮች በመቅረፍ ረገድም የማይተካ ሚና እንደሚኖረው አቶ ከበደ አክለው ተናግረዋል፡፡(አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top