Connect with us

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ በሀሰተኛ ዘገባዎች አዝኛለሁ አለ

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ በሀሰተኛ ዘገባዎች አዝኛለሁ አለ
Photo: Facebook

ዜና

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ በሀሰተኛ ዘገባዎች አዝኛለሁ አለ

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን በቀረበው ሀሰተኛ ዘገባ ማዘኑን ገለፀ።

ተቋሙ የሚሰበስበውን ገንዘብ አለአግባብ ጥቅም ላይ አውሏል በሚል በአንዳድ የመገናኛ ብዙሃን የቀረበው የተሳሳተ ዘገባ እንዳሳዘነው ለኢዜአ በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡

ትረስት ፈንዱ የፋይናንስ አሠራር እና ደንብ ያልተከተለ ምንም አይነት የገንዘብ አጠቃቀም አሁንም ሆነ ለወደፊቱ እንደማይኖር አረጋግጧል፡፡

ተቋሙ ከ25 ሺህ በላይ ለጋሾች 6.36 ሚሊዮን ዶላር ከሰበሰበው 1.173 ሚሊዮን ዶላር ለወረርሺኙ መከላከል የሚውሉ የህክምና ዕቃዎች ገዝቶ ወደ ሀገር ቤት መላኩን ጠቁሟል፡፡

በዚህም መሰረት ተቋሙ የሚሰበስበውን ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ ብቻ በማዋል ብክነትንና ስርቆትን ለመከላከል የሚያስችል ስርአት መዘርጋቱን አስታውቋል፡፡

ኢዜአ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top