Connect with us

የትኛውም ኃይል የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ማስቆም እንደማይችል ተገለፀ

የትኛውም ኃይል የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ማስቆም እንደማይችል ተገለፀ
Photo Facebook

ዜና

የትኛውም ኃይል የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ማስቆም እንደማይችል ተገለፀ

የትኛውም ኃይል የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ማስቆም እንደማይችል ተገለፀ::

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር እንዲሳለጥ ዕዙ ፈርጀ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የምዕ/ዕዝ ም/አዛዥ ለሎጀስቲክ ክቡር ብ/ጄ ተስፋየ ተመስገን ተናገሩ፡፡

ጄኔራል መኮንኑ በግድቡ አካባቢ ፀጥታን የማረጋገጥ ስራዎች በመስራት ላይ የሚገኙትን የሰራዊት አባላት በጎበኙበት ወቅት እንደተናገሩት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እንደ ሀገር ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ህዝባችን ፍፃሜውን በከፍተኛ ትኩረት የሚከታተለውን ይህን ፕሮጀክት ሰራዊታችንም በንቃት እየጠበቀው ይገኛል ብለዋል፡፡

የፀጥታ ስራውን ይበልጥ ለማጠናከር የዕዙ ኮማንድ ያልተቋረጠ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ የገለፁት ጄኔራል መኮንኑ የግንባታ ሒደቱን በቅርበት የሚከታተለው ሰራዊታችን ውጤቱን እየተመለከተ ስለሚገኝ ለተሰጠው ተልዕኮ እንደ ተደማሪ አቅም ሆኖታል ብለዋል፡፡

ብ/ጄ ተስፋየ ተመስገን የትኛውም ኃይል የታላቁ ህዳሴ ግድብ የግንባታን ማስቆም እንደማይችል ጠቁመው ሰራዊታችንም በከፍተኛ እልህና ሞራል የተጣለበትን ሃላፊነት ከመወጣት ባሻገር ለሰባተኛ ጊዜ በወር ደመወዙ የቦንድ ግዥ መፈፀሙን አውስተዋል፡፡

ምንጭ:- የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top