Connect with us

አየር መንገዱ የካርጎ ጭነት አገልግሎቱን ለህክምና ቁሳቁስ ማጓጓዣነት በስፋት አሰማራ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ ጭነት አገልግሎቱን ለህክምና ቁሳቁስ ማጓጓዣነት በስፋት አሰማራ
Photo Facebook

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

አየር መንገዱ የካርጎ ጭነት አገልግሎቱን ለህክምና ቁሳቁስ ማጓጓዣነት በስፋት አሰማራ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ ጭነት አገልግሎቱን ለህክምና ቁሳቁስ ማጓጓዣነት በስፋት ማሰማራት መጀመሩን ገለፀ።

አየር መንገዱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫው፥ በዓለም ላይ የተከሰተውን የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን ተከትሎ የጭነት ማጓጓዣ (ካርጎ) አውሮፕላን ፍላጎት በዓለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይህንን በግምት ውስጥ በማስገባት ያለውን አቅም በሙሉ ተጠቅሞ የአውሮፕላን የጭነት አገልግሎት (ካርጎ) በሚያስፈልግበት ቦታ ሁሉ ለማዳረስ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

በአፍሪካ ትልቁ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ እና የሎጂስቲክስ አገልግሎት በአሁኑ ወቅትም “ፋርማ ዊንግ” በሚል ልዩ አገልግሎትም በአፍሪካ እና በሌሎች የዓለም ሀገራትም የህክምና ቁሳቁስ የማጓጓዝ ስራ እየሰራ መሆኑንም ነው የገለፀው።

በተጨማሪም የህክምና ቁሳቁስን ለማከማቸት የሚያስችል የሙቀት መቆጣጠሪያ የተገጠመለት 54 ሺህ ስኩዌር ሜትር ላይ ባረፈው መጋዝኑም የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን የማከማቸት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑንም ነው ያስታወቀው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅትም የሙቀት መጠናቸው መጠበቅ ያለባቸው ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን ኪሎግራም በላይ የህክምና ቁሳቁሶችን እያጓጓዘ መሆኑንም አስታውቋል።

የተለያዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች፣ ለጋሽ ሀገራት እና ሊሌች በዘርፉ የሚሰሩ አካላት የህክምና ቁሳቁሶችን ለአፍሪካ እና ለሌሎች የዓለም ሀገራት አዲስ አበባን እና የኢትዮጵያ አየር መንገድን እንደ ማእከል ለመጠቀም መወሰናቸውም ይታወሳል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም፥ አየር መንገዱ በዓለም ላይ በኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ላይ የተለያዩ የህይወት አድን የህክምና ቁሳቁሶችን በማጓጓዝ የበኩሉን እየተወጣ መሆኑን ገልፀው፤ “በዚህ አስቸቸጋሪ ወቅት ዓለምን ለማገልገል በመቻላችን ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል” ብለዋል።

(ምንጭ :-ፋና)

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top