Connect with us

መንግሥት በሚያቀርበው የምግብ ዘይት ላይ በሊትር 4 ብር ከ30 ሣንቲም የዋጋ ጭማሪ አደረገ

መንግሥት በሚያቀርበው የምግብ ዘይት ላይ በሊትር 4 ብር ከ30 ሣንቲም የዋጋ ጭማሪ አደረገ
Photo Facebook

ኢኮኖሚ

መንግሥት በሚያቀርበው የምግብ ዘይት ላይ በሊትር 4 ብር ከ30 ሣንቲም የዋጋ ጭማሪ አደረገ

መንግሥት በሚያቀርበው የምግብ ዘይት ላይ በሊትር 4 ብር ከ30 ሣንቲም የዋጋ ጭማሪ አደረገ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆነው ህብረሰተብ ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዳይደርስበት ከውጪ ሃገራት በድጎማ ከሚያስገባቸው ምርቶች ውስጥ አንዱ የምግብ ዘይት መሆኑን የተናገሩት የኢፌ.ዲሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የጥራት እና ሬግላቶሪ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እሼቴ አስፋው የዚህም ምርት የመሸጫ ዋጋ የሚወሰነው በዓለም ገበያ መሰረት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚህም መሰረት መንግስት በድጎማ ከወጪ የሚያስገባው የምግብ ዘይት ካሁን ቀደም ሲሸጥ ከነበረበት ዋጋ ከሚያዚያ 6 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በሊትር የ4 ብር ከ30 ሳንቲም ጭማሪ መደረጉን እና ዘይት ለማቅረብ ከክልሎች ተወክሎ የመጣ ማንኛውም አስመጪ ድርጅት በዚህ ዋጋ ለአከፋፋዮችና ለቸርቻሪዎች ማስረከብ እንደሚጠቀበቅበትም ተናግረዋል፡፡

ቸርቻሪዎች ከአስመጪዎች የተረከቡትን ምርት በተመሳሳይ ዋጋ ብር 4፡30 (አራት ብር ከሳንቲም ሰላሳ) በመጨመር ለህብረተሰቡ ሽያጭ መፈጸም እንደሚገባቸው ሚኒስትር ዴኤታው የተናገሩ ሲሆን ከዚህ ዋጋ ውጪ ግብይት ሲፈጽም በተገኘ ማንኛውም የንግድ ማህበረሰብ ላይ መንግስት እርምጃ ይወስዳል ብለዋል፡፡

ስለዚህ መንግስት ካስቀመጠው ዋጋ ውጪ ምርቱ ሲሸጥ ከተገኘ ህብረተሰቡ ለሚመለከታቸው የከተማ አስተዳደር፣ ለክልል የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮዎች እና ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ሚኒስትር ዴኤታው ጥሪ አቅርበዋል፡፡(ንኢሚ)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top