Connect with us

ዩናይትድ ስቴትስ ለአለም የጤና ድርጅት የምትጠውን መዋጮ አቋረጠች

ዩናይትድ ስቴትስ ለአለም የጤና ድርጅት የምትጠውን መዋጮ አቋረጠች
Photo: GAGE SKIDMORE/FLICKR (CC BY-SA 2.0

ዜና

ዩናይትድ ስቴትስ ለአለም የጤና ድርጅት የምትጠውን መዋጮ አቋረጠች

ዩናይትድ ስቴትስ ለአለም የጤና ድርጅት የምትጠውን መዋጮ አቋረጠች

ዩናይትድ ስቴትስ ለአለም የጤና ድርጅት የምትሰጠውን መዋጮ እንደምታቋርጥ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታወቁ።

ባለፉት ቀናት በተደጋጋሚ የጤና ድርጅቱ ስራውን በአግባቡ አልተወጣም በማለት ወቀሳ ሲሰነዝሩ የነበሩት ትራምፕ ዛቻቸውን አሁን እውን አድርገዋል።

ትራምፕ በኋይት ሀውስ ግቢ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ « የኮሮና ተህዋሲን ለመግታት በተወሰደው ደካማ ርምጃ እና መሸፋፈን ላይ » የአለም የጤና ድርጅት የነበረው ሚና እስኪጣራ ድረስ ክፍያው እንዲቆም ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተናግረዋል።

እንደ ትራምፕ ከሆነ የአለም የጤና ድርጅት በቻይና በሚያገኘው መረጃ ላይ ብቻ ተመርኩዞ ርምጃ በመውሰዱ ተህዋሲው በመላው ዓለም ሊሰራጭ ችሏል። ድርጅቱም በፈፀማቸው በርካታ ስህተቶች «ለብዙ ሰዎች ሞት» ተጠያቂ ነው ብለዋል።

መቀመጫውን ጄኔቫ ሲውዘርላንድ ላደረገው የአለም የጤና ድርጅት ዮናይትድ ስቴትስ ከፍተኛውን ገንዘብ የምትሰጥ ሀገር ናት። ባለፈው ዓመት ዩናይትድ ስቴትስ 400 ሚሊዮን ዮ ኤስ ዶላር ለድርጅቱ ከፍላለች።

ትራምፕ በአሁኑ ሰዓት በድርጅቱ ላይ የወሰዱትን ርምጃ አግባብ ነው ትላላችሁ? DW

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top