Connect with us

ከነገ ጀምሮ ለ400 ሺህ የአዲስአበባ ነዋሪዎች የምግብ ድጋፍ ይደረጋል

ከነገ ጀምሮ ለ400 ሺህ የአዲስአበባ ነዋሪዎች የምግብ ድጋፍ ይደረጋል
Photo: Social media

ዜና

ከነገ ጀምሮ ለ400 ሺህ የአዲስአበባ ነዋሪዎች የምግብ ድጋፍ ይደረጋል

ከነገ ጀምሮ ለ400 ሺህ የአዲስአበባ ነዋሪዎች የምግብ ድጋፍ ይደረጋል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ400 ሺህ ነዋሪዎች የምግብ ፍጆታ ስርጭት ሊጀመር ነው።

የከተማ አስተዳደሩ ከ1ሺህ200 በላይ የምግብ ባንኮችን አዘጋጅቶ ከለጋሽ አካላት የተሰበሰበ የምግብ ፍጆታን እያከማቸ ይገኛል።

በባንኮቹ የተከማቸው የምግብ ፍጆታም እስካሁን ለተለዩት ከ400 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከነገ ሐሙስ ጀምሮ የማሰራጨት ስራ ለመጀመር እየተሰራ ይገኛል፡፡

በክፍለ ከተማው በመጀመሪያ ዙር ለተለዩ ነዋሪዎች እስከ ሶስት ወር ድረስ በየወሩ እንደየ ቤተሰባቸው ብዛት ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡

የምግብ ስርጭቱን በአግባቡ እና በፍትሃዊነት ለማከናወን በየወረዳዎች እና የመንደር ብሎኮች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃዎችን የሚለዩ እና የሚያከፋፍሉ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እና የልየታ ኮሚቴዎች ተዘጋጅተው የመለየት ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

Continue Reading
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top