Connect with us

የሚኒስትሯ ተማፅኖ!..”የደም እጥረት ገጥሞናል”

የሚኒስትሯ ተማፅኖ!.."የደም እጥረት ገጥሞናል"
Photo: Social media

ዜና

የሚኒስትሯ ተማፅኖ!..”የደም እጥረት ገጥሞናል”

በአሁኑ ጊዜ በሃገራችን የኮሮና ቫይረስ በሽታ(COVID-19) ወረርሽኝ እንዳይስፋፋ የህዝብ እንቅስቃሴ መገደብ የበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ቁጥር መቀነስ ሃገራዊ የደም ክምችቱ ላይ እጥረት እያስከተለ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል፡፡

በዚህ ወረርሽኝ ወቅት በቂ የደም አቅርቦትን ማረጋገጥ እጅግ አስፈላጊ መሆኑንና በተለይ በወሊድ ወቅት የሚፈጠረው የደም መፍሰስ፣ የድንገተኛ አደጋ እንዲሁም የካንሰር ህመምተኞች የሚያጋጥማቸው የደም እጥረት ለመቅረፍ የበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ደም እንዲለግሱ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ አያይዘውም ደምና የደም ተዋፅኦዎች በተፈጥሮ ባላቸው አጭር የመጠቀሚያ ጊዜ ምክንያት በመደበኛነት የደም ማሰባሰብ ስራዎችን መስራት አስፈላጊ እንደሆነና ለዚህም በሃገሪቱ የሚገኙ ደም ባንኮች በሙሉ የደም ማሰባሰብ ስራዎችን አጠናክረው ለመስራት እየሞከሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የደም ማሰባሰቡ ስራ በባህሪው ብዙ ሰው የሚሰበሰብበት ቢሆንም ደም አሰባሰቡ ስራ አስፈላጊውን የጤና ደህንነት ጥንቃቄ እና ማህበራዊ መራራቅን የተከተለ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የደም ማሰባሰቡ ስራ ቀልጣፋ እንዲሆን የሞሃ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ለብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል፡፡ (ኢዜአ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top