Connect with us

የምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማ ተማፅኖ

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማ ተማፅኖ
Photo Facebook

ዜና

የምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማ ተማፅኖ

ተማፅኖ

አከራዮችን ምሕረት ጠየቁ

የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማ (ኢንጂነር) በአነስተኛ ንግድ የተሠማሩ ነጋዴዎችና ቤተሰቦቻቸው በእንቅስቃሴ መቀነስ እንዳይጎዱ አከራዮች የኪራይ ምሕረት እንዲያደርጉላቸው ጠየቀ፡፡

‘‘የጊዜውን ፈተና፣ በጊዜው ብልሃት እና ጸሎት ታግለን ለማለፍ ስንለፋ አንዳንድ የግድ የሆኑ መሠዋዕትነቶች ይደቀናሉ’’ ያሉት ምክትል ከንቲባው አከራዮች ጥቂት የገንዘብ መሠዋዕትነት በመክፈል ሕይወት እንዲታደጉ ጠይቀዋል።

‘‘እንቅስቃሴ በመቀነሳችን በተለይ ጥቂት ነገር ሸቅጦ በልቶ ለማደር ደጅ ደጅ የሚያዩ አነስተኛ ንግድ የሚሠሩ ወገኖች ከነቤተሰባቸው በእጅጉ ይጎዳሉ፤ ለእነዚህ እና ተጎዱ ለምንላቸው እስኪ እናስብላቸው፤ ዛሬን ከነልጆቻቸው እንዲያልፉ ማገገሚያ እንዲሆን የኪራይ ክፍያ እንተውላቸው ዘንድ እነሆ ተማፅኖዬ ለአከራዮች ሁሉ ይድረሳችሁ’’ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

አከራዮች ፈጣን አወንታዊ ምላሽ እንደሚሰጡም ተስፋ ማድረጋቸውን ምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማ መግለጻቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top