Connect with us

የዶክተር ዐብይ መልዕክት ~ ለወጣቶች

የዶክተር ዐብይ መልዕክት ~ ለወጣቶች
Photo: Social media

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

የዶክተር ዐብይ መልዕክት ~ ለወጣቶች

የዶክተር ዐብይ መልዕክት ~ ለወጣቶች

ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ከኢቢኤስ ቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ ለወጣቶች ምሳሌ ጠቅሰው ያስተላለፉት መልዕክት ተመችቶኛል።

አንድ ወጣት አንድ ጀነራል ቤት ግድግዳ ላይ የተሰቀሉ የተለያዩ ሜዳሊያዎችና ሽልማቶች ይመለከትና ይኸን ሁሉ ሽልማት ያገኙት ምን ሰርተው ነው ሲል ይጠይቃቸዋል። (ቃል በቃል የተወሰደ አለመሆኑን አንባቢ ይረዳልኝ)

ጀነራሉም ለወጣቱ ውሀ የሞላ ብርጭቆ ሰጥተውት ይኸን ብርጭቆ በመያዝ ተራራውን ዞረህ ከመጣህ ምስጢሩን እነግርሀለሁ። ስትጓዝ የብርጭቆ ውሀው ጠብ ካለ አልሞ ተኳሾች ስላሉ ይገድሉሀል፤ ተጠንቀቅ ይሉትና ይሸኙታል።

ወጣቱ በጥንቃቄ እየተራመደ ብርጭቆውን እንደያዘ በሰላም ተራራውን ዞሮ ይመለሳል። በኃላም ጀነራሉ መንገድ ላይ የገጠመው ነገር እንዳለ ይጠይቁታል።

ወጣቱም የብርጭቆ ውሀ እንዳይፈስበት በመስጋት ሙሉ ትኩረቱ ብርጭቆው ላይ ስለነበር ምንም ነገር መንገድ ላይ እንዳላየ መለሰላቸው።

ጀነራሉም የእኔም ሽልማት ምስጢር ይኸው ነው። ሥራዬ ላይ ሙሉ በሙሉ አተኩሬ ስሰራ በመኖሬ የተገኘ ነው አሉት።

እናም ጠ/ሚኒስትሩ ወጣቱ በተሰለፈበት ሙያው ሙሉ በሙሉ ትኩረት ቢያደርግ ውጤታማ ይሆናል የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።(ጫሊ በላይነህ)

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top