Connect with us

የኢትዮጵያ ሊቃውንት እውቀትን የሚደብቁት ወትሮም ቸኩሎ የሚጠፋ ትውልድ ገጥሟቸው ነው

የኢትዮጵያ ሊቃውንት እውቀትን የሚደብቁት ወትሮም ቸኩሎ የሚጠፋ ትውልድ ገጥሟቸው ነው
Photo Facebook

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

የኢትዮጵያ ሊቃውንት እውቀትን የሚደብቁት ወትሮም ቸኩሎ የሚጠፋ ትውልድ ገጥሟቸው ነው

የባህል ሊቃውንቶቻችን ሙከራ እውን ለማድረግ ራሳችንን ጠብቀን ለእኛ የደከሙትን ድካም ለፍሬ እናብቃው፤
****
ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

የሀገር በቀል ሊቃውንቶቻችን ድብቆች ናቸው ተብለው ይታማሉ፤ በእርግጥም ባይደበቅ በሚያልቅ ትውልድ መካከል የሚኖሩ በመሆናቸው ዝምታቸው ጥበብ አላዋቂ መሳይነታቸው ትውልድን መታደግ ነው፡፡

እንደ ሀኪም አበበች ያሉ ጠበብት ሀገራቸው ኢትዮጵያ ሆነ እንጂ ሌላው ዓለም ቢሆኑ ዛሬ ዓለምን ለታደገ ውጤት በበቁ፤ ኢትዮጵያ ብዙ ሊቆቿን ወደ መቃብር በሸኘች ቁጥር ራሷ ወደ መቃብር እየወረደች እንደሆነ ሳታውቅ ዛሬ እጇን ለምዕራባውያኑ የዘረጋች ጠባቂ ሀገር ሆናለች፡፡

በኢትዮጵያ የባህል ህክምናን ለጭንቅ ቀን መጠቀም፤ ቀን ሲያልፍ ቅጠል ብጠሳና ድብትርና እያሉ ማጣጣል፤ የበቁትን ሊቃውንት ጠንቋይ ባለ ዛርና መሰል ቅጽል ስሞች መስጠት የቻይናንና የህንድን የእጽዋት መድሃኒቶች ከፋብሪካ ሲወጡ ተቀብሎ ለመቃም አስገድዶናል፡፡

የኛ ሊቃውንት ብዙውን ነገር ግልጽ አያደርጉም፡፡ ምክንያታቸው ይታወቃል ጫፍ ይዞ የሚሮጥ ቆንጽሎ የሚሞት ዜጋ ብዙ ስለሆነ ነው፡፡ የሀኪም አበበችና የባልደረቦቻቸው ጥረት ጥሩ መንገድ ላይ ነው፡፡ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እያለፈ ነው፡፡

ውጤቱ ተስፋ ሰጪ ነው፤ ግን አልተመረተም፣ አልተከፋፈለም፤ ገና ግኝት ነው፡፡ ግኝት ለውጤት እስኪበቃ በህይወት ኖሮ መጠቀም ተርፎ ከመድሃኒቱ መገናኘት ያስፈልጋል፡፡

የባህል ሀኪሞቹ ለትውልድ ህይወት መከራቸውን አይተዋል፤ ትውልዱ ግን ለራሱ ህይወት መከራውን ማየት እየደለም አረፍ ብሎ ቤቱ መቀመጥን የአድዋ ዘመቻ ያክል መከራ ሆኖበታል፡፡ ምቾትን ሽሽት መከራን መጋፈጥ የፈለገ ትውልድ ጫፍ ይዞ ይተነትናል፡፡ መድሃኒቱ ተገኘ የሚሉት ዜናዎች ከአራት ሰዓት በኋላ ኤች አይ ቪ የለም ብሎ ያለቀውን ትውልድ ሊያስታውሰን ይገባል፡፡

አሁን ይሄንን ድካም እውን ለማድረግ ኢትዮጵያ የዓለም ፈውስ ሆና ለመመልከት የሚፈልግ የሊቃውንቶቻችን አጋር ራሱን ጠብቆ ተጨማሪ ጭንቀት አልባ የሚከራና የጥናት ጊዜን ለባለሙያዎቹ መስጠት ይኖርበታል፡፡ ያ ከሆነ እንድናለን፤ የባህል ሀኪሞቻችን ምክር ሁሌም ቤት መቀመጥን፣ ራስን ማድመጥን አደብ መግዛትን ይሻልና፤

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top