Connect with us

“ጸጥ ብለህ ሥራህን ሥራ”

"ጸጥ ብለህ ሥራህን ሥራ"

ጥበብና ባህል

“ጸጥ ብለህ ሥራህን ሥራ”

“ጸጥ ብለህ ሥራህን ሥራ”
(ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት)

በዚህ ዘመን ውኃ ከማጠጣት ስለ ውኃ አጠጣጥ መናገር፣ ለእገሌ ቤት ከመስጠት ለእገሌ ቤት ስጡት ብሎ መናገር፣ ቆሻሻውን ከማጽዳት ቆሻሻው ይጽዳ ብሎ መጻፍ እንደ ትግል ይቆጠራል፡፡

እሳቱ ላይ ተጥዳ ከምትጠበሰው ጋጋሪ በላይ የእሳቱን ፎቶ የሚለጥፈው ተቃጠልኩ ይላል፡፡ ቅቤ አንጣሪው ተቀምጣ ስለ ቅቤ አነጣጠር ተናጋሪው ምች መታኝ ይላል፡፡

በዚህም የተነሣ ከሚሠሩ ይልቅ ስለ ሥራ የሚናገሩ ሰዎች እየበዙ ነው፡፡ እኛም አፈር ዝቀውና ገደል ሞልተው መንገዱን ከሚሠሩት ይልቅ ስለ መንገዱ የሚጮኹትንና የሚዘግቡትን ቦታ ሰጥተናቸዋል፡፡

ይህም ሠሪዎችን አሳንሶ አውሪዎችን እንዳያበዛቸው ያሠጋል፡፡ ከኳስ ተጨዋቹ ይልቅ ስለ ኳስ የሚናገረው ትልቁን ቦታ ከያዘ፣ ከሮጠው በላይ ስለ ሩጫው ያወራው ከተከበረ ‹አህያ ወደቤት ውሻ ወደ ጓሮ› የተባለው ደርሷል ማለት ነው፡፡

ጸጥ ብለህ ሥራህን ሥራ፣ ጩኸቱን ሥራህ ይጩህልህ Work Hard In Silence and Let Success Make the Noise. የሚል አባባል አለ፡፡ በጩኸት ከመሥራት በሥራ መጮኽ የተሻለ ነው የሚል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጥበብና ባህል

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top