Connect with us

የፌዴራሊስት ኃይሎች ከፎረም ወደጥምረት ራሱን አሳደገ

የፌዴራሊስት ኃይሎች ከፎረም ወደጥምረት ራሱን አሳደገ

ዜና

የፌዴራሊስት ኃይሎች ከፎረም ወደጥምረት ራሱን አሳደገ

ህወሓትን በአባል ያቀፈው የፌዴራሊስት ኃይሎች ፎረም ራሱን ወደ ጥምረት ለማሳደግ የሚያስችለውን ስምምነት ከሳምንት በፊት ማካሄዱ ተሰማ፡፡

በመቀለ ከተማ ከሳምንት በተካሄደው ሥነሥርዓት ላይ ሕወሓትን በመወከል የጥምረቱ ሰነድ ላይ የፈረሙት የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል መሆናቸው ተሰምቷል፡፡

የምርጫ ቦርደ ታዛቢ በተገኘበት በተከናወነው በዚሁ የጥምረት ፊርማ ሥነሥርዓት ጎን ለጎን በተጓደሉ የአመራር አባላት ምትክ ምርጫ መከናወኑም ተሰምቷል፡፡ በዚሁ መሠረት ልጅ መስፍን ሽፈራው- ከመኢብን የጥምረቱ ዋና ጸሐፊ ሆነው ሲመረጡ አቶ ገብሩ በርሄ የፋይናንስ ኮምቴ ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ጥምረቱ 25 አባላትን ማቀፉንም ምንጫችን ገልጾአል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የፎረሙ ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ትግስቱ አወሉ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ ከፌዴራሊስት ሃይሎች ፎረም ራሳቸውን ማግለላቸውን ማስታወቃቸው አይዘነጋም፡፡ አቶ ትግዕስቱ እንዳሉት የፌዴራሊስት ሃይሎች በሚል የተሰባሰበው ሃይል ህወሓት ዳግም የበላይነቱን ለመመለስ የሚያደርገው ጥረት አካል ነው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top