Connect with us

በአሜሪካ በአባይ ግድብ የድርድር ሒደት ለግብፅ መወገኗን የሚቃወም የሠላማዊ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ ተጠራ

በአሜሪካ በአባይ ግድብ የድርድር ሒደት ለግብፅ መወገኗን የሚቃወም የሠላማዊ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ ተጠራ
Photo: Anadolu Agency

ዜና

በአሜሪካ በአባይ ግድብ የድርድር ሒደት ለግብፅ መወገኗን የሚቃወም የሠላማዊ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ ተጠራ

የትራምኘ አስተዳደር በአባይ ጉዳይ በጀመረው የማደራደር ሀላፊነት ለግብፅ መወገኑን በመቃወም በመጪው ሐሙስ ታላቅ ሠላማዊ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ እንደሚካሄድ የሰልፉ አስተባባሪዎች ገለፁ።

እንደአስተባባሪዎቹ ገለፃ ከዉጭ በሚመጣ ተፅኖ መተባበር መቻቻል አንድ ሆኖ ድል መቀዳጀት ልምዳችን ነዉና ዛሬ ነገ ሳንል ለዉድ ሃገራችን ኢትዮጵያ አንድ መሆን የዉዴታ ግዴታም ነዉ።

የአሜሪካ መንግስት በአባይ ግድብ ድርድር ዙሪያ በኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን አድሏዊ ጫና እንድታቆምና ከአደራዳሪነቷ እንድትወጣ ለመጠየቅና በሉአላዊነታችን ላይ የተቃጣውን ጣልቃ ገብነት ለመቃወም በተዘጋጀው ሰልፍ ላይ ሁላችንም በጋራ እንድንገኝ እንጠይቃለን ብለዋል።

ቦታ፦ State Department

2201 C St NW

Washington, DC. 20520

ቀን፦ ሐሙስ (February 27, 2020)

ሰአት፦ 9:00 AM

የዲሲ ግብረ ሃይል፣ መደመር በተግባር፣ የትውልድ ድልድይ (ስለአባይ ግድብ ተቆርቋሪ አስተባባሪዎች)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top