Connect with us

የቢራ እና የለስላሳ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ጨመረ

የቢራ እና የለስላሳ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ጨመረ
Stock image

ኢኮኖሚ

የቢራ እና የለስላሳ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ጨመረ

የኤክሳይዝ ታክስ መፅደቅ ተከትሎ በተለይ በአዲስ አበባ ከትላንት ጀምሮ የችርቻሮ ዋጋ ጨመረ። በዚህ መሰረት የመደበኛ ቢራ ዋጋ በጠርሙስ በአማካይ ከ17 ብር ወደ23 ብር እና ከዚያ በላይ ሲጨምር የአንድ ጃምቦ ድራፍት ዋጋ በአማካይ ከ15 ብርወደ 22 ብር አድጓል።የለስላሳ መጠጦች በጠርሙስ በአማካይ ከ12ወደ 15 ብር ጭማሪ አሳይቷል።

ድሬቲዩብ ያነጋገራቸው የግሮሰሪ ባለቤቶች እንደተናገሩት የድራፍት የአንድ በርሜል ዋጋ ከብር 818 ወደ 1ሺ 60 ሲያድግ የአንድ ሳጥን ቢራ ዋጋ ከ290 ወደ 430 አድጓል።የለስላሳ ምርቶች በሳጥን ከ170 ወደ 240 ብር ማደጉን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ የአልኮል ምርቶችም ዋጋ መጨመሩ ታውቋል። ከዚህ በፊት ስራ ላይ የነበረውን የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ በመተካት አዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ በፓርላማ የፀደቀው የካቲት 5 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑ ይታወሳል።

አንድ አዋጅ ተግባራዊ የሚሆነው በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣ በኋላ ሲሆን የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ ታትሞ ሳይወጣ የገቢዎች ሚኒስቴር ከየካቲት 6 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ማድረጉን መግለፁ አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል።

በሌላ በኩል በህግና በስርዓት የማይመራው ገበያ የአልኮልና ለስላሳ ምርቶች ዋጋ መጨመር ተከትሎ የዋጋ ንረት ሊያሳይ ይችላል የሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ ተፈጥሯል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top