Connect with us

ኢትዮጵያ ወረርሽኞችን የመከላከል ዝግጁነት ዓለም አቀፍ ጥምረትን ተቀላቀለች

ኢትዮጵያ ወረርሽኞችን የመከላከል ዝግጁነት ዓለም አቀፍ ጥምረትን ተቀላቀለች
Photo: Facebook

ጤና

ኢትዮጵያ ወረርሽኞችን የመከላከል ዝግጁነት ዓለም አቀፍ ጥምረትን ተቀላቀለች

ኢትዮጵያ በምርምር ውጤቶች የታገዘ ወረርሽኞችን የመከላከል ዝግጁነት ዓለም አቀፍ ጥምረትን ከአፍሪካ አገሮች ቀዳሚ በመሆን መቀላቀሏን በይፋ አስታወቀች፡፡

በአፍሪካ ህብረት የጎንዮሽ ውይይት መድረክ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳስታወቁት የኢትዮጵያ መንግስት ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን፣ ከአፍረካ የበሽታ መቆጣጠር ማዕከል እና በምርምር ውጤቶች የታገዘ ወረርሽኞችን የመከላከል ዝግጁነት ዓለም አቀፍ ጥምረት ጋር በመተባበር መድረኩ እንደተዘጋጀ ገልጸው ኢትዮጵያ የጥምረቱ አባልነትን በይፋ መቀላቀሏ ወቅቱ የሚጠይቀው አንገብጋቢ ጉዳይ በመሆኑን ከጥምረቱ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ጄኔራል ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክትም በድንገት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለመከላከል አፍሪካዊያን ሃገራት ዝግጁነታቸውን ማጠናከር ወቅቱ አሁን መሆኑን ጠቁመው ይህ በማድረጋቸውም ዜጎቻቸውን እንደ ኮሮናቫይረስ፣ ሳርስ፣ ሜርስ፣ ኢቦላ፣ ላሳ ፊቨር ካሉ አዳዲስ በሽታዎች ለመከላከል ፈጣን ምላሽ መስጠት እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ጥምረቱን በአባልነት ስትቀላቀል አገሪቱ የሚከሰቱባትን ወረርሽኞች በቀላሉ መከላከል የሚያስችላትን የምርምር አቅሟን ለማጠናከር በጥምረቱ ከፍተኛ ተጠቃሚ እንደምትሆን ነው የገለጹት፡፡

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የአፍሪካ አገሮች ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑ ክትባቶችን ከውጭ በማስገባት ይጠቀማሉ፡፡

በምርምር ውጤቶች የታገዘ ወረርሽኞችን የመከላከል ዝግጁነት ጥምረት እ.ኤአ በ2017 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን ዓላማውም የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለመከላከል አዳዲስ የምርምር ውጤቶችን በመጠቀም ክትባቶችን የመፍጠር፣ የማምረትና ለዜጎች ጥቅም እንዲውሉ የሚያስችል አቅምን ማጠናከር ነው፡፡

የአፍሪካ አገሮች ድንገት ከሚከሰቱ የወረርሽኝ በሽታዎች መከላከል የሚያስችላቸውን ዝግጁነትን ማጠናከር እንዲሚገባቸውና በዚህም በራሳቸው የምርምር አቅም ክትባቶችን በማምረት የዜጎቻቸውን ህይወት ለመታደግ የሚያስችላቸውን አቅም ለማጠናከርና ለማበረታታት መድረኩ እንደተዘጋጀ መገለፁን ከሚኒስቴሩ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top