Connect with us

በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ ወደ ሥራ የገቡ ኢንቨስትመንቶች በ 99 በመቶ አሽቆለቆለ

በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ ወደ ሥራ የገቡ ኢንቨስትመንቶች በ 99 በመቶ አሽቆለቆለ
Photo: Capital

ኢኮኖሚ

በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ ወደ ሥራ የገቡ ኢንቨስትመንቶች በ 99 በመቶ አሽቆለቆለ

በብሄራዊ ባንክ የሚወጣው የየሩብ አመት የኢኮኖሚ መግለጫ (ቡለቲን) በ2012 በጀት አመት የመጀመሪያው ሩብ ወደ ስራ የገቡ ኢንቨስትመንቶች 9 ብቻ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

ይህም ከ 2011 ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 554 ኢንቨስትመንት አንፃር የ98 ነጥብ 3 በመቶ ቅናሽ የታየበት ነው፡፡

በተመሳሳይ በመጀመሪያው ሩብ አመት ወደስራ ለገቡ ፕሮጀክቶች ኢንቨስት የተደረገው የብር መጠን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት በ99 በመቶ አንሶ 60 ነጥብ 7 ሚሊየን ብቻ መሆኑን ሰነዱ ያብራራል፡፡ በባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ኢንቨስት የተደረገው 5 ነጥብ 88 ቢሊየን ብር ነበር፡፡

በሌላ በኩል በሩብ አመቱ ወደ ስራ ከገቡት 9 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች አንዱ ትግራይ ሲሆን ቀሪው በአዲስ አበባ ነው፡፡ ሆኖም አንድም የውጭ ኢንቨስትመንት በተጠቀሰወው ግዜ ወደ ስራ አልገባም፡፡

በ2011 የመጀመሪያው እሩብ አመት ወደ ስራ ከገቡ 554 ኢንቨስትመንቶች ስድስቱ በውጭ አልሚዎች የተያዙ እና 199 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸው ነበሩ፡፡

አምና በተመሳሳይ ወቅት በአማራ እና ኦሮሚያ በቅደም ተከተላቸው 40 እና 123 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸው አንድ አንድ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ ገብተው የነበረ መሆኑን የሚያሳየው ሰነዱ ዘንድሮ ግን ዜሮ መሆኑን ያሳያል፡፡ (ካፒታል ጋዜጣ)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top