Connect with us

የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ለኮሮና ቫይረስ መድሃኒት ምርምርና ህክምና የሚውል 100 ሚሊዮን ዶላር ለገሰ

የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ለኮሮና ቫይረስ መድሃኒት ምርምርና ህክምና የሚውል 100 ሚሊዮን ዶላር ለገሰ
Photo: GETTY

ጤና

የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ለኮሮና ቫይረስ መድሃኒት ምርምርና ህክምና የሚውል 100 ሚሊዮን ዶላር ለገሰ

የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ለኮሮና ቫይረስ መድሃኒት ምርምርና ህክምና የሚውል 100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለግሷል።

ፋውንዴሽኑ ድጋፉን ያደረገው የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስን ወረርሽኝ ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት የ675 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ርብርብና ድጋፍ መጠየቁን ተከትሎ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መሆኑንና እስካሁን 24 ሺህ ሰዎች መጠቃታቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ከቻይና ውጭ በቫይረሱ የተጠቁ 190 ኬዞች ብቻ መኖራቸው የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር እድሉ መኖሩን ጠቅሰዋል።

በድጋፍ መልክ የሚገኘው ገንዘብ በዋናነት ችግሩ በተከሰተባቸው ሀገራት ያለውን የህክምና ሁኔታ ለማሻሻል እንደሚውል ነው ድርጅቱ ያስታወቀው።

ሰሞኑን በቻይና ተከስቶ በተለያዩ ሀገራትም ጭምር የተሰራጨው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እስካሁን 490 የሚሆኑ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ ሲሆን ከ24 ሺህ በላይ ሰዎች ላይ ታይቷል።

ምንጭ፡-ፎርብስ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top