Connect with us

የኮንዶሚኒየም ቤቶችን መገበያየት እንጂ ካርታ ማዘዋወር እንደማይቻል አስተዳደሩ ማገዱ ተሰማ

የኮንዶሚኒየም ቤቶችን መገበያየት እንጂ ካርታ ማዘዋወር እንደማይቻል አስተዳደሩ ማገዱ ተሰማ
Photo: Facebook

ዜና

የኮንዶሚኒየም ቤቶችን መገበያየት እንጂ ካርታ ማዘዋወር እንደማይቻል አስተዳደሩ ማገዱ ተሰማ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጋራ መኖሪያ ቤቶችን መገበያየት (መሸጥና መግዛት) ቢቻልም፣ የባለቤትነት ሰነድ (ካርታ) ስም ማዘዋወር እንዳይቻል ዕግድ መጣሉ ተሰማ፡፡

አምስት ዓመታትና ከዚያ በላይ ያስቆጠረ የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤት፣ ቤቱን መሸጥ የሚከለክለው እንደለሌለና መብቱም እንደሆነ፣ ነገር ግን ቤቱን የገዛው አካል የቤት ባለቤትነት መብቱን (ካርታውን) ስም ማዞር ማግኘት እንዳይችል (እንዳይዘዋወርለት) ላልተወሰነ ጊዜ መታገዱን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ መሬት ልማት አስተዳደር የኮንዶሚኒየም ቤቶች የባለቤትነት ሰነድ ስም ማዘዋወር እንዳይቻል ዕግድ የጣለው፣ የቀበሌ ቤቶች የባለቤትነት ሰነድ (ካርታ) እየተዘጋጀ በመሆኑና እስከሚጠናቀቅ ድረስ በየክፍላተ ከተሞች ባለው የሥራ ጫና መሆኑን ምንጮች ተናግረዋል፡፡ የቀበሌ ቤቶች ካርታ ተሠርቶ እንደተጠናቀቀ መደበኛና ማንኛውም ቤትንና ንብረትን በሚመለከት መከናወን ያለበት ሥራ በመደበኛነት እንደሚቀጥል የተገለጸ ቢሆንም፣ ዕግዱ ሌላ ምክንያት እንዳለውም የሪፖርተር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ምንጩ ያልታወቀ ከፍተኛ ገንዘብ እየተዘዋወረና በአስተዳደሩም ሆነ በባለሥልጣናት ጥርጣሬ ሳያድር እንዳልቀረ የገመቱት ምንጮች፣ በከተማው ውስጥ በዕጣ የተላለፉና አምስት ዓመታት ያለፋቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በመግዛት፣ በአንድ የቤት ቁጥር በርከት ያሉ የቀበሌ መታወቂያዎች ይወጣሉ የሚል ሥጋትም እንዳለም ጠቁመዋል፡፡

ይህ ደግሞ በቀጣይ በሚካሄደው ምርጫ ላይ የራሱ ተፅዕኖ ስላለው ያንን ለመቆጣጠርና ለመከላከል መሆኑንም ግምታቸውን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ነባር መታወቂያ ያላቸው ነዋሪዎች ካልሆኑ በስተቀር አዲስ መታወቂያ መስጠት መቆሙ ይታወሳል፡፡

ዕግድ ተጥሎበታል ስለተባለው የኮንዶሚኒየም ቤት የባለቤትነት ሰነድ (ካርታ) ስም ማዘዋወር የታገደበት ምክንያት ምን እንደሆነና እስከ መቼ እንደሚቆይ ማብራሪያ ለማግኘት፣ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዎችን ለማግኘት የተደረገው ጥረት አዲስ ምደባ ላይ እንደሆኑ በመግለጹ ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት አልተቻም፡፡(ምንጭ:- ሪፖርተር – ታምሩ ፅጌ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top