Connect with us

ያልተዘመረላቸው ጀግኖቻችን!!

ያልተዘመረላቸው ጀግኖቻችን!!
Photo: Facebook

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ያልተዘመረላቸው ጀግኖቻችን!!

ያልተዘመረላቸው ጀግኖቻችን!! | (ጫሊ በላይነህ በድሬቲዩብ)

ዛሬ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም፤ ኢትዮጵያ የራሷን ሳተላይት ወደ ህዋ የላከችበት ልዩና ታሪካዊ ቀን ነው፡፡ እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላችሁ!! ያው ይኸንኑ ዜና አስመልክቶ የሚሰጡ መግለጫዎች ላይ እንደዝንጀሮ የበሰለውን አድነው መብላት በሚወዱ አንዳንድ ፖለቲከኞች ምክንያት የዚህ ስኬት ቁልፍ ሰዎችን ሆን ብለው መዝለላቸው አሳዝኖናል፡፡ እነሱ ሊያዳፍኑት ቢሞክሩም እውነት ጮክ ብላ መናገርዋ አይቀርም፡፡

አቶ ተፈራ ዋልዋ እና የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አልአሙዲ ልፋት እነሆ ጮክ ብለን እንናገራለን፡፡

የብአዴን መስራችና ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ ተፈራ ዋልዋ በጡረታ ዘመናቸው ከሰሩት ድንቅ ሥራዎች መካከል የኢትዮጵያን የስፔስ ሳይንስ ወደፊት ለማራመድ ሳይታክቱ መሥራታቸው ነው፡፡

ከአንድ ዓመት በፊት ዓለም አቀፉ የአስትሮኖሚ ህብረት ጠቅላላ ጉባዔውን በኦስትሪያ ቬና ሲያካሂድ አቶ ተፈራ ዋልዋን በኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅ እና አሁን ላለበት ደረጃ እንዲደርስ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ዓለም አቀፍ እውቅና ከከፍተኛ ክብር ጋር የሰጣቸው ለዓመታት ያደረጉት ጥረት በመገንዘቡ ነበር፡፡

እነአቶ ተፈራ ዋልዋ፣ ነፍሳቸውን ይማረውና እነዶ/ር ለገሰ ወትሮ ስለስፔስ ሳይንስ አብዝተው ባወሩ ቁጥር በወቅቱ በሥልጣን ላይ የነበረው የህወሓት መራሹ ኢህአዴግ ጥቂት የማይባሉ ሹማምንቶች እንደሥራ ፈት ይቆጠሩ ነበር፡፡ እናም ዓላማቸውን ትንሽም እንኳን ፈቅ ለማድረግ በፋይናንስ እጦት እግራቸው መላወስ ባቃተበትና ከጃንሜዳ እንኳን ተሆኖ በቴሌስኮፕ ሰማይን ለማየት የሚያስችል አቅም ለመፍጠር የነበራቸው ትንሽዬ ምኞት ማሳካት ተቸግረው ነበር፡፡ በዚያ አስቸጋሪ ወቅት የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ ደግሞ “ለኢትዮጽያ ነፍሴንም ቢሆን እሰጣለሁ” ብለው ከጎናቸው ቆሙ፡፡ ምን ይህ ብቻ እነተፈራ ዋልዋ ወጪው ከባድ ከመሆኑ አንጻር ፈርተው ትንሽዬ ቴሌስኮፕ እንዲገነባ የጠየቁትን “ይኸማ ለኢትዮጵያ አይመጥንም” በሚል ውድቅ አድርገውና አስጠንተው የጀርመን ስሪት የሆኑ ሁለት ቴሌስከኮፖች (እያንዳንዳቸው አንድ ዲያሜተር ሌንስ ያላቸው) እንዲሰራ እና ወደአገር እንዲገባ በማድረግ ታሪክ ሰርተዋል፡፡

በተጨማሩም ለሰው ኃይል ሥልጠና እና የእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ ማዕከልን ለማቋቋምና በቁሳቁስ ለማሟላት በድምሩ ወደ 100 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ወጪ አድርገዋል፡፡

በዚህ ያልተጠበቀ ድጋፍ የተበረታቱት የማህበሩ የበላይ ጠባቂ በመሆን እያለገሉ ያሉት አቶ ተፈራ ዋልዋ የእንጦጦ ኦብዘርባቶሪን ከማቋቋምም በተጨማሪ የሕዋ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ በመንግስትም የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ እንዲካተት ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በአሁን ወቅት ኢትዮጵያ በእንጦጦ ኦብዘርባቶሪ ባስገነባቻቸው ሁለት ቴሌስኮፖች ምርምር ማድረግ ከመቻሉም በላይ በዛሬው ዕለት የራሷን ሳተላይት ለማምጠቅ የበቃቸው በእነተፈራ እና በእነሼህ አልአሙዲ የላቀ አስተዋጽኦ ነውና ለዚህ ተግባራቸው ከአንገታችን ዝቅ ብለን ከበሬታችን እንሰጣቸዋለን፡፡ ልፋታችሁን የኢትዮጵያ አምላክ ይካስ!

አቶ ተፈራ ዋልዋ በአንድ ወቅት በሚድሮክ ለሚታተመው ጥረት መጽሔት እንዲህ አሉ፡፡ “የእንጦጦን የህዋ ሳይንስ ተቋም ለመገንባት ትልቅ ራዕይ ያመጣውና የደገፈው ሼህ ሙሐመድ አል-አሙዲ ነው። ሙሐመድ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው።”
በመጨረሻም ጀግኖቹን አቶ ተፈራ ዋልዋ እና የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለን እላለኹ፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top