Connect with us

የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ሽልማት!

የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ሽልማት!

ዜና

የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ሽልማት!

ፓን አፍሪካ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ኔትወርክ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ላደረጉት የሰብአዊ መብት ተከራካሪነት በትላንትናው ዕለት በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል የዕውቅና ሽልማት አበርክቶላቸዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን ከሕመማቸው ጋር እየታገሉ ለተደረገላቸው ክብር አመስግነዋል፡፡

አፈንዲ ሙተቂ የተባሉ ጸሐፊ ስለፕሮፌሰር መስፍን የሰብዓዊ መበት ተሳትፎ በአንድ ወቅት እንዲህ ጽፈው ነበር፡፡ “በሰኔ 1983 የተመሰረተው የሽግግር መንግሥት ያጸደቀው ቻርተር በኢትዮጵያ ውስጥ የሃሳብና የመደራጀት ነጻነት መፈቀዱን አብስሮ ነበር፡፡ በዚህም መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚያ በፊት ባልታየ መልኩ እንደ አሸን ፈሉ፡፡ ህብረ ብሄራዊና ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ተመሰረቱ፡፡ በአንጻሩ ደግሞ “ሰብዓዊ መብት” የሚል ለብዙዎች እንግዳ የሆነ ጽንሰ-ሃሳብ በሚዲያ መንሸራሸር ጀመረ፡፡

አብዛኛው ምሁር ከአንዱ የፖለቲካ ቡድን ጋር ራሱን አቆላለፈ፡፡ የዘመኑ እንግዳ ደራሽ የሆነውን የሰብዓዊ መብት ጽንሰ-ሃሳብ የሚያብራራ ሰው ግን ጠፋ፡፡ በዚህ መሀል ነው ታላቁ ኢትዮጵያዊ ምሁር ብዙዎች የረሱትን የሰብዓዊ መብት አጀንዳ በማንሳት ለህዝቡ ግንዛቤ ለማስጨበጥና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በማስረጃ ለመሞገት የተነሱት፡፡ እርሳቸው ያቋቋሙት ድርጅትም ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ጠበቃ በመሆን ያሳለፈው ውጣ ውረድ እንዲህ በቀላሉ የሚገለጽ አይደለም፡፡…”

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top