Connect with us

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ሊገጥሟት የሚችሉ አራት ሴናሪዮዎች ይፋ ተደረጉ

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ሊገጥሟት የሚችሉ አራት ሴናሪዮዎች ይፋ ተደረጉ

ዜና

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ሊገጥሟት የሚችሉ አራት ሴናሪዮዎች ይፋ ተደረጉ

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ሊገጥሟት የሚችሉ አራት ሴናሪዮዎች ይፋ ተደረጉ።

አራቱ ሴናሪዎች /እጣ ፈንታ/ ይፋ የተደረጉት ትናንት ማምሻውን (ህዳር 23/2012 ዓ.ም) በስካይላይት ሆቴል “የምንፈልጋት ኢትዮጵያ በ2032” በሚል ርእስ በተደረገዉ የዉይይት መድረክ ላይ ነዉ ።

በመድረኩ ላይ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች ፣፣ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ሀገር አቀፍ እና ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ፣የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

የዴስቲኒ ኢትዮጵያ በአገሪቱ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አክቲቪስቶች፣ ክልሎች፣ ሲቪል ማኅበራት፣ የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ፣ የሚዲያ ባለሙያዎች እና ምሑራን የተውጣጡ 50 ሰዎች በጥንቃቄ በመምረጥ ላለፉት ስድስት ወራት ዝግ ስብሰባዎችን በማካሄድ ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት አገራችን ሊገጥሟት የሚችሉ አራቱን ሴናሪዎች መቅረፁን የዴስቲኒ ኢትዮጵያ አስተባባሪ አቶ ንጉሴ አክሊሉ ተናግረዋል ።

አራቱ ሴናሪዎች አፄ በጉልበቱ ፣ ሰባራ ወንበር ፣ የፋክክር ቤት እና ንጋት ናቸዉ ።

በመድረኩ ላይ የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ይህን ሴናሪዮ ለማዘጋጀት የተነሱ ግለሰቦችን፣ የተለያዩ የፖለቲካ አቋም ይዘዉ በሃሳብ አንድነት ተሰባስበዉ ለሴናሪዮ ሃሳብ ያዋጡ 50 ሰዎችን አመስግነዋል ።

ሳይቸግረን የቸገረን ራስን በሌላዉ ቦታ አስቀምጦ መየት ነዉ ያሉት ክብርት ሚኒስትሯ፤ ይህን ሴናሪዮ ያዘጋጁ አካላት አብሮ በመቀራረብ ዉስጥ ያለ ሃይልን አሳይተዉናል ብለዋል ።

ከአራቱ ሴናሪዮ (እጣ ፈንታዎች) ውስጥ ለኢትዮጵያ “ንጋት” እንደሚመኙ የገለፁት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ለዚህም ነገን ዛሬን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል ።

የሴራኒዮ አባላት ያሳለፏቸዉን ዉጣ ዉረድና የቀጣይ ምኞታቸዉን ከ1-3 ደቂቃ እየተሰጣቸዉ ሃሳባቸዉን ማካፈላቸውን የስላም ሚኒስቴር አስታውቋል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top