Connect with us

የኢትዮጵያ እና የዩጋንዳ የቢዝነስ ፎረም በካምፓላ ተካሄደ

የኢትዮጵያ እና የዩጋንዳ የቢዝነስ ፎረም በካምፓላ ተካሄደ

ኢኮኖሚ

የኢትዮጵያ እና የዩጋንዳ የቢዝነስ ፎረም በካምፓላ ተካሄደ

ዩጋንዳ ካምፓላ የሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ ከዩጋንዳ ንግድ ኢንዱስትሪ ማህበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ እና የዩጋንዳ የቢዝነስ ፎረም ዛሬ ህዳር 19 ቀን 2012 ዓም ካምፓላ በሚገኘው ፐርል ኦፍ አፍሪካ ሆቴል ተካሂዷል።

በፎረሙ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ፐብሊከ ዲፕሎማሲ ልኡክ አባል እና የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ሊቀመንበር ኢንጅነር መላኩ አዘዘው በኢትዮጵያ ያለ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጨችን በተመለከተ በምስል የተደገፈ ገለጻ አድርገዋል።

በተመሳሳይ የዩጋንዳ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ኦሊቭ ኪጎንጎ በዩጋንዳ ያሉ ምቹ የንግድና የኢንቨስትመንት እድሎችን በተመከተ በምስል የተደገፈ ገለጻ አድርገዋል።

ገለጻውን ተከትሎ ውይይት ተደርጓል። በውይይቱም ኢትዮጵያ እና ዩጋንዳ በድንበር የማይዋሰኑ ከመሆናቸውም በላይ ወደብ አልባ አገሮች በመሆናቸው እርስ በእርስ ለመገበያየት የተለያዩ ተግዳሮቶች እያጋጠማቸው መሆኑ ተነስቷል።

ከተገዳሮቶቹ መካከልም ከትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶች፣ ከቋንቋ ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙ ችግሮች፣ ከኢትዮጵያ አኳያ ጊዜያዊ የውጭ ምንዛሬ እጥረት መኖር፣ ከሁለቱ አገሮች የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶች፣ ረጅምና የተንዛዛ አላስፈላጊ ቢሮክራሲና መሰል ችግሮች መኖራቸው በውይይቱ በስፋት ተነስቷል።

በተነሱት ያቄዎች ላይ ገለጻውን ከሰጡት የሁለቱ አገሮች የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ፕሬዝዳንቶች እና ከተሳታፊዎች ማበራሪያና ምለሽ ተሰጥቷል። ሁለቱ አገሮች የጀመሩትን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት አጠናክረው ሲቀጥሉ ከግብይት ጋር በተያየዘ ያሉ ተግደሮቶቸ በሂደት እየተቀረፉ እንደሚሄዱም ተገልጿል።

በዛሬው ፎረም ከሁለቱም ወገን ከ100 በላይ ባለሀብቶች ተሳትፈዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት
ህዳር 19 ቀን 2012 ዓ.ም

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top