Connect with us

የእስራኤል ተመራማሪዎች አዲስ የስኳር በሽታ ህክምና ማግኘታቸውን ይፋ አደረጉ

የእስራኤል ተመራማሪዎች አዲስ የስኳር በሽታ ህክምና ማግኘታቸውን ይፋ አደረጉ
Photo: Facebook

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

የእስራኤል ተመራማሪዎች አዲስ የስኳር በሽታ ህክምና ማግኘታቸውን ይፋ አደረጉ

የእስራኤል ተመራማሪዎች አዲስ የስኳር በሽታ ህክምና ዘዴ ማግኘታቸውን ይፋ አደረገዋል።

የስኳር ህመም የሚከሰተው ሰውነታችን ለኑሮም ሆነ ለእድገት የሚያስፈልገውን ስኳር በትክክል ለመጠቀም ሳይችል ሲቀር መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

አንድ ሰው ለስኳር ህመም ተጠቂ ነው የምንለው በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ከፍ ብሎ ሲገኝ ሲሆን፥ ይህም ሰውነታችን ኢንሱሊን የተሰኘውን ሆርሞን በበቂ ሁኔታ ወይም ጭራሹኑ እንዳያመነጭ ያደርገዋል።

የእስራኤል ተመራማሪዎች ሰሞኑን ይፋ ባደረጉት ጥናት የስኳር ህመምን ለማከም የሚስችል አዲስ የህክምና ዜዴ ማግኘታቸው አስታውቀዋል ።

እንደ ተመራማሪዎች ገለፃ አዲሱ የህክምና ዘዴ ታማሚዎችን በቀን ቋሚ በሆነ ስዓት ሶስት ጊዜ የተመጣጠነ ምግብ እንዲመገቡ ማድረግ በሽታውን በቀላሉ ለመከላከል ያስችላል።

ይህም የታማሚዎችን የክብደት መጠን፣ የምግብ ፍላጎት፣ ዕለታዊ የኢንሱሊን እና የሄሞግሎቢን ኤ 1 ሲ ፍጆታን ለመቀነስ የስችላል ነው የተባለው።

በአሁኑ ወቅት በዓለማችን 20 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች ዓይነት 1 የስኳር በሽታ ስላለባቸው ለመኖር መደበኛ የሆነ የኢንሱሊን መርፌየሚያስፈልጋቸው መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል ፡፡

ዓይነት 2 የስኳር በሽታ ዓይነት ያለባቸው 54 ሚሊዮን ሰዎች ግን አልፎ አልፎ ሲብስባቸው ካልሆነ በስተቀር ኢንሱሊንን እምብዛም አይጠቀሙም፡፡

ስለሆነም የኢንሱሊን የመድሃኒት አምራች ኩባንያዎች መደበኛውን ዓይነት ኢንሱሊን እንዲያመርቱ በማድረግ ጥራት እና ደህንነቱን ካረጋገጠ በኋላ በተመጣጣኝ ዋጋ ለተገልጋዮች ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑ ተነግሯል።

ምንጭ፡- ሺንዋ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top