Connect with us

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ካፒቴን ሺፈራው ገብሬ ወልደ ሰማያትን አመሰገነ

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ካፒቴን ሺፈራው ገብሬ ወልደ ሰማያትን አመሰገነ
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ካፒቴን ሺፈራው ገብሬ ወልደ ሰማያትን አመሰገነ

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አረንጓዴ አሻራቸውን ለማኖር የገቡትን ቃል በማክበር ሰሞኑን በአዲስ አበባ በጀሪካን ውኃ ጭነው እየተዘዋወሩ ሲያጠጡ የታዩትን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀድሞ አብራሪ ካፒቴን ሺፈራው ገብሬ ወልደ ሰማያትን አመሰገነ፡፡

ካፒቴን ሺፈራው ባለፉት ሦስት ወራት ሲንከባከቧቸው የቆዩትን ከቦሌ ሚካኤል እስከ ወሎ ሰፈር የተተከሉ ችግኞችን ውኃ ሲያጠጡ መታየታቸውን የገለፀው ፅ/ቤቱ በአካባቢው ሲያልፍ ምስሉን በስልኩ በማስቀረት ይህንን በጎ መልእክት በማኅበራዊ ሚዲያ ያካፈለውን ሔኖክ ሚናስንም አመስግኗል፡፡

መልካም ዜግነትን ማጎልበትና እንዲህም ለሚያደርጉ ምስጋና ማቅረብ ሊያድግ የሚገባው ባህል ነው ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የምንፈልጋትን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ፣ ለመጪው ትውልድ የተሻለውን ለማቆየት ተስፋ ሳንቆርጥ እንትጋ ! ሲል መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top