Connect with us

ወይዘሮ ትልቅ ሰው ለአማራ ክልል የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ትልቅ ስጦታ ሰጡ

ወይዘሮ ትልቅ ሰው ለአማራ ክልል የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ትልቅ ስጦታ ሰጡ

ኢኮኖሚ

ወይዘሮ ትልቅ ሰው ለአማራ ክልል የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ትልቅ ስጦታ ሰጡ

ወይዘሮ ትልቅ ሰው ለአማራ ክልል የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ትልቅ ስጦታ ሰጡ። ባህር ዳር ግራንድ ሆቴል ከስድስት ወር በኋላ ራድሰን ብሉ ይኾናል። ሄኖክ ስዩም በድሬቲዮብ

የኢትዮጵያ የሆቴል ኢንዱስትሪ እንደ ፓለቲካው መዲናዋን ሙጥኝ ያለ ነው። የኢትዮጵያ ቱሪዝም ደግሞ አክሱም ላሊበላ ባሌ ጎንደር ባህር ዳር ጅንካና ዳሉልን በመሳሰሉት አካባቢዎች የሚገኝ ነው። እርግጥ አዲስ አበባም ቢኾን ዓለም አቀፍ ብራንድ ያላቸው ሆቴሎች ብርቅ ናቸው።

ባህር ዳር ከስድስት ወር በኋላ የራድሰን ብሉ ሆቴል መገኛ ትኾናለች። ይኼ ትርጉሙ ብዙ ነው። ከየትም የዓለም ክፍል ወደ ጣና ዳር የሚመጣ እንግዳ ፓርስና ለንደን እንደማጠብቁት ዓይነት ሆቴል አንዱ ይጠብቀዋል። የ

ቀድሞው ግራንድ ሆቴል ባለቤት ወይዘሮ ትልቅ ሰው ገዳሙ እና ራድሰን ብሉ ትናንት አዲስ አበባ በሚገኘው ራድሰን ብሉ ስምምነቱን ተፈራርመዋል።

በኦዚ ኢንተርናሽናል በኩል በአቶ ቁምነገር ተከተል የተመራው ራድሰንን ባህር ዳር የማስገባትና ግራንድ ሆቴልን ራድሰን የማድረግ ጥረት ሁለት ዓመት መፍጀቱን በስምምነት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ተመስገን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ክብርት ዶክተር ሂሩት ካሳውን ጨምሮ በርካታ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ባለ ሀብቶችና የሆስፒታሊቲው ኢንዱስትሪ መሪዎች በተገኙበት የተካሄደው የፊርማ ሥነ ሥርዓት ላይ አሁን በስራ ላይ የሚገኘው ግራንድ ሆቴል በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ዝግ ይኾናል።

በስድስት ወራትም ሆቴሉን መልሶ የማደራጀት ሥራ ይሰራል። የመለዮ ስያሜው አርማውና ገፅታው ይቀየራል። ከስድስት ወራት መልሶ የማደራጀት ሥራ በኃላ በራድሰን ብሉ ማኔጅመንት የሚመራው የባህር ዳር ራድሰን ብሉ ሆቴል እውን ይኾናል። ይኼ ለአማራ ክልል የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ትልቅ አቅም ነው። እንደ ሀገርም ሌላው ዓለም በሚመራበት የሆቴል ኢንዱስትሪ ጥበብ ለመጓዝ መነሳሳትን ይፈጥራል።

የጣና ዳሯ ፈርጥ የትም ዓለም ስሙ ከሚጠራው የንግድ ስያሜ የተቆራኘ የሆቴል ባለቤት ትኾናለች። ለዚህ ይመስለኛል ባለሃብቷ ለወሰኑት ውሳኔ ደስታቸውን መግለፅ የፈለጉትና በአቶ ወርቁ አይተነው አሰባሳቢነት በርቺ ማለት እንፈልጋለን ያሉ ባለሃብቶች ለወይዘሮ ትልቅ ሰው የሬንጅሮቨር መኪና ስጦታ ያበረከቱት።

ወይዘሮ ትልቅሰው ገዳሙ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማሩ ባለ ሀብት ሲኾኑ በማርቆስ እና በጋምቤላም ተመሳሳይ የሆቴል ዘርፍ ላይ ኢንቨስት አድርገዋል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top