Connect with us

ኢትዮጵያውያን ከኬንያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

13 ኢትዮጵያውያን ከኬንያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
Photo: Facebook

ዜና

ኢትዮጵያውያን ከኬንያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በኬንያ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ ከኬንያ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን ጥቅምት 29 ቀን 2012 ዓ.ም 13 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል።

ኢትዮጵያወያኑ ከተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ተታለው ያለምንም የጉዞ ሰነድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ በሞያሌ በኩል ድንበር አቋርጠው ወደ ኬንያ ሲገቡ ነበር በህግ ጥላ ስር የዋሉት።

ዕድሜያቸው ከ16 እስከ 23 ዓመት የሚሆነው እነዚህ መጣቶች በህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎቹ የተሳሳተ መረጃ በመታለል ያለምንም የጉዞ ሰነድ እና ገንዘብ በመክፈል ከሀገራቸው የወጡ ሲሆን የተነገራቸው እና ያጋጠማቸው ነገር እንደማይገናኝና ወደ ሀገራቸው በመመለስ ሌሎች ወገኖቻቸው የዚህ ህገወጥ ሰዎች ዝውውር ሰለባ እንዳይሆኑ ማስተማር እንደሚፈልጉ ገልፀዋል፡፡

ኤምባሲው በፍርድ ቤት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን የጉዞ ሰነድ በማዘጋጀት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አደርጓል፡፡

ኤምባሲው ባለፉት ጥቂት ወራት በተመሳሳይ መንገድ ለእስር ተዳርገው የነበሩ 86 ወገኖቻችንን ወደ ሀገር ቤት መልሷል።

ምንጭ:-  በናይሮቢ የኢፌዲሪ ኤምባሲ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top