Connect with us

የጤና ሚኒስቴር የኢንፌክሽን መከላከያና መቆጣጠሪያ አዲስ መመሪያ አወጣ

የጤና ሚኒስቴር የኢንፌክሽን መከላከያና መቆጣጠሪያ አዲስ መመሪያ አወጣ
Photo: Facebook

ጤና

የጤና ሚኒስቴር የኢንፌክሽን መከላከያና መቆጣጠሪያ አዲስ መመሪያ አወጣ

በታዳጊ አገራት በሚገኙ የጤና ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት ከሚሄዱ 100 ታካሚዎች ውስጥ አሥር ያህሉ ህክምና ሲያገኙ ለኢንፌክሽን እንደሚጋለጡ ዓለም አቀፍ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

በኢትዮጵያ በሚገኙ የጤና ተቋማት ህክምና ለማግኘት በሚሄዱ ተገልጋዮች ላይ በኢንፌክሽን የመያዝ እድልን ለመቀነስ ብሎም ለማጥፋት ባለፉት 3 ዓመታት በጤና ሚኒስቴር ሲዘጋጅ የቆየው የኢንፌክሽን መከላከያና መቆጣጠሪያ መመሪያ ዛሬ ይፋ ተደርጓል፡፡

በአገሪቱ በጤና ተቋማት ላይ ኢንፌክሽንን መከላከል ዋንኛ ችግር መሆኑን በሚኒስቴሩ የሜዲካል አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ያቆብ ስማን ተናግረዋል፡፡

መመሪያው በጤና ተቋማት የህክምና አገልግሎት ሲሰጥ የሚፈጠሩ ኢንፌክሽኖችን በመከላከል የህሙማንን ደህንነትን ለመጠበቅ የሚያስችልና ለችግሩ የመፍትሄ ሀሳቦችን ጭምር ያካተተ ነው ብለዋል፡፡

በጤና ተቋማት የሚከሰት ኢንፌክሽንን ለመከላከል የሚረዳውን ይህን አዲሱን መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን የተለያዮ የጤና ተቋማት ገልፀዋል፡፡

(ምንጭ:- ኢቲቪ)

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top